Jossy Kassa - Alebegn Tezeta paroles de chanson

paroles de chanson Alebegn Tezeta - Jossy Kassa




አዝ፦ እኔ የማይረሳኝ ውለታ
አለብኝ አንድ ትዝታ
ቀራንዮ መስቀሉ ላይ
ሞቶ ያዳነኝ
እኔን ለማዳን ነው የደም ላብ ያላበህ የሞትክልኝ
ተሰቃየህልኝ መርገሜን ወሰድከው ልታድነኝ
ልጅህ ነኝ በጣር የወለድከኝ ሕይወትና ሰላም የሆንከኝ
በሞትህ እኔን ስታድነኝ አየሁ የመስቀሉ ፍቅርህን
(አልረሳውም እኔ) ለኔ የዋልክልኝ አለብኝ ውለታ
(አልረሳውም እኔ) ተሰቃየህልኝ ሞትክልኝ ጎልጎታ
(አልረሳውም እኔ) ዘመኔን በሙሉ አንተን ባመልክህ
(አልረሳውም እኔ) ምክንያቴ ይሄ ነው የመስቀል ፍቅርህ
አዝ፦ እኔ የማይረሳኝ ውለታ
አለብኝ አንድ ትዝታ
ቀራንዮ መስቀሉ ላይ
ሞቶ ያዳነኝ
አምላክ ሆነህ ሳለህ ሲያንገላቱህና ሲያፌዙብህ
እንደወንጀለኛ አስረው ሲገርፉህስ መች ራሩልህ
ሲንቁህ ሲሳበቁብህ መልስም አልነበረህ ሲወግሩህ
ለኔ ነው ይህ ሁሉ የሆነው እንዴት እንድትወደኝ እንዳየው
(አልረሳውም እኔ) ለኔ የዋልክልኝ አለብኝ ውለታ
(አልረሳውም እኔ) ተሰቃየህልኝ ሞትክልኝ ጎልጎታ
(አልረሳውም እኔ) ዘመኔን በሙሉ አንተን ባመልክህ
(አልረሳውም እኔ) ምክንያቴ ይሄ ነው የመስቀል ፍቅርህ
ለኔ ነው ለኔ
በመስቀል ላይ የሞተው ስለኔ



Writer(s): Simone Tsegay


Jossy Kassa - Teneshina Abrie, Vol. 2
Album Teneshina Abrie, Vol. 2
date de sortie
23-11-2010



Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.
//}