Jossy Kassa - Geze Alew Lehulu paroles de chanson

paroles de chanson Geze Alew Lehulu - Jossy Kassa



ቃልህን ሰምቼ ተጽናናሁኝና
ይፈጸማል ብዬ ነገን ጠበቅኩና
ጊዜው ሲገፋ አስጨነቀኝ
ያልከኝም ምንም አልሆነልኝ
ይልቁን መከራ ሆነብኝ
ምንድነው ጉዱ መላ በሉኝ
ወተትና ማርን የምታፈስ ሀገር
አወርሳችኋለሁ ብለህ ለእስራኤል [1]
መንገድ ሲጀምሩ መከራቸው በዛ
የተናገርካቸው ሁሉ እስኪረሳ [2]
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ
መች በረሃ ቀሩ ቃሉ ተፈፀመ
አትዘገይም አንተ ያልከው ሁሉ ሆነ [3]
ምንም ብትዘገይም ትመጣለህና
እጠብቅሃለሁ የእኔም ቀን አለና
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ
አንተ ያልከኝ ሌላ ነው
የሚሆንብኝ ሌላ ነው
ምንድነው ነገሩ ወዴት ነው
ሚስጥሩ አስተምረኝ
አዝ፦ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ኧረ ነፍሴ ረጋ በዪልኝ
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ያደርገዋል እርሱ ካለኝ
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ሳይፈፀም ጊዜው ቢገፋም
(ጊዜ አለው ለሁሉም) እጠብቃለሁ የትም አልሄድም
ዮሴፍ ወንድሞቹ ሲሰግዱለት፡ አየ
እንደምታከብረው እንዲነግስ አለመ [4]
ነገር ግን ሲነሳ ሊገድሉት ተነሱ
በግዞት ተጣለ ህልሞቹም ተረሱ [5]
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ
ዘመናት ቢፈጅም ህልሙ ተፈጸመ
የማይሆን ቢመስልም እንዳየው ግን ሆነ
በለሱን የሚጠብቅ ፍሬዋን ሊበላ
ለታገሱ ሁሉ ጊዜ አለህና
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ
አንተ ያልከኝ ሌላ ነው
የሚሆንብኝ ሌላ ነው
ምንድነው ነገሩ ወዴት ነው
ሚስጥሩ አስተምረኝ
አዝ፦ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ኧረ ነፍሴ ረጋ በይልኝ
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ያደርገዋል እርሱ ካለኝ
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ሳይፈፀም ጊዜው ቢገፋም
(ጊዜ አለው ለሁሉም) እጠብቃለሁ የትም አልሄድም
አምላኬ ጊዜው ሲሄድብኝ መላ ፍለጋ
አጋር ቤት ገብቼ እንዳልጐዳ
አስተዋይ አርገኝ ትዕግስትን ስጠኝ
ጌታዬ አንተን ተስፋ አድርጌ አላፍርምና
በራስህ ጊዜ ይሆናልና
እባክህ እርዳኝ ታጋሽ አርገኝ



Writer(s): Simone Tsegay


Jossy Kassa - Teneshina Abrie, Vol. 2
Album Teneshina Abrie, Vol. 2
date de sortie
23-11-2010



Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.