Mesfin Gutu - Ante Yene paroles de chanson

paroles de chanson Ante Yene - Mesfin Gutu



አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ
ባስጨናቂው እለት ለኔ ደርሰህ
በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ
ታሪኬን ለውጠህ
ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የእኔ
አንተ የኔ የራሴ የግሌ የእኔ
ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ
በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ
ታሪኬን ለውጠህ
ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ
ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከእኔ (አንተን ከእኔ)
ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከእኔ (ኦ አንተን ከእኔ)
ተማመለህ እኮ ነው የኔ ጌታ
በጭንቅ የወለድከኝ በጎልጎታ
እድሜዬን በሙሉ ሰጥሃለሁ
ዘላለም ለቃልህ እገዛለሁ እገዛለሁ
ታዲያ ልዘምር እንጂ
ልቀኝ እንጂ
ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ
ታዲያ ታዲያ
ታዲያ ልዘምር እንጂ
ልቀኝ እንጂ
ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ
እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል
እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል
እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል
እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል
ማንጋት ልማድህ ነውና
ማንሳት ልማድህ ነወና
ማክበር ልማድህ ነወና
ማስዋብ ልማድህ ነውና
ውዴ የኔ ነው እኔም ደግሞ የእርሱ ነኝ የኢየሱስ ነኝ
ውዴ የኔ ነው እኔም ደግሞ የእርሱ ነኝ የኢየሱስ ነኝ
ማንም አይገባም በመሀላችን
ጉድለት የሌለበት ነው ፍቅራችን
ጊዜም ሁኔታም አይሽረዉም ለእኔስ ኢየሱሴ ልዩ ነዉ (ልዩ ነዉ)
ታዲያ ልዘምር እንጂ
ልቀኝ እንጂ
ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ
ታዲያ ታዲያ
ታዲያ ልዘምር እንጂ
ልቀኝ እንጂ
ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ
አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ
ባስጨናቂው እለት ለኔ ደርሰህ
በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ
ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የእኔ




Mesfin Gutu - Elif Elif, Vol. 3
Album Elif Elif, Vol. 3
date de sortie
25-08-2004




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.