Rophnan - Piyasa Lay paroles de chanson

paroles de chanson Piyasa Lay - Rophnan



ትዝ ይለኛል እንደ ትላንት መጀመሪያ ቀን ሳያት
ያኔ ቬል ሱሪው ነገር አፍሮ በጠር በጠር በጠር
ካዲስ ከተማ በቶሎ ኣይ በቶሎ ጉዞዬ ቤቴ 4 ኪሎ ኣይ 4 ኪሎ
ልጅት ነች ናዝሬት school ናዝሬት school
መንገዷ ባራዳ በኩል ኤኤኤኤ
በግርግሩ መሀል ተያየን እኔና እሷ ያኔ ተገናኘን
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ትዝ ይለኛል አይኔ ካይንሽ መጀመሪያ ስተዋወቅሽ
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደ ላይ
አዲስ አበባን ሳያት ሰባዎቹ መሀል
ትዝ ይለኛል ብዙ ነገር ሮሀ እና ያንቺ ፍቅር
አባትሽ ጀነራል-ያ ጀነራል
አስሮ ሲገርፍ ወንድሜን- ወንድሜን
እኔና አንቺ ግን አልፈናል- አዎ አልፈናል
ፍቅርን ባላንጦች መሀል
አስታውሳለሁ መጽ-ሀፍቶቹን ሳመጣልሽ
ሀዲስ, ባዕሉ, ሎሬት ፀጋዬን ካራዳው ስር ብለን ተቀጣጥረን
አውቶብሷ ሳትመጣ በግሬ እቀድማት ነበር
በግርግሩ መሀል ላይሽ ካራዳው ስር አንቺን ላገኝሽ
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
አይረሳም ጥንቱ ነገር ያሳለፍነው ደጉ መንደር
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ
ታሪክ ያለው እጅ ወደ ላይ
ጨዋታው ጨዋታው ካራዳው ቦታ
ጨዋታው ጨዋታው ካራዳው ቦታ
ሳሚልኝ ቤቱን ጊዬርጊስን አዬ
ሳምኩልህ ቤቱን ጊዬርጊስን አዬ
ጥምቀት ነው ጨዋታ ካራዳው ቦታ
ጥምቀት ነው ጨዋታ ካራዳው ቦታ
ሸኘሁ ታቦቱን አድዋ ዘማቹን አዬ
ሸኘሁ ታቦቱን አድዋ ዘማቹን አዬ
ዘራፍ ዘራፍ...
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ (ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ)
አይረሳም የጥንቱ ነገር (ው-ው)
ያሳለፍነው ከደጉ መንደር (ው-ው)
ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ (ፒያሳ ላይ ፒያሳ ላይ)
ታሪክ ያለው እጅ ወደ ላይ
ጨዋታ ጨዋታ
ካራዳው ቦታ
(ጨዋታ ጨዋታ)
(ካራዳው ቦታ)
ሳሚልኝ ቤቱን
ጂዬርጊስን አዬ-ዬ
(ሳምኩልህ ቤቱን)
(ጊዬርጊስን አዬ-ዬ)
ጥምቀት ነው ጨዋታ
ካራዳው ቦታ
(ጥምቀት ነው ጨዋታ)
(ካራዳው ቦታ)
ሸኘሁ ታቦቱን
አድዋ ዘማቹን አዬ
(ሸኘሁ ታቦቱን)
(አድዋ ዘማቹን አዬ)
ዘራፍ ዘራፍ
(ና ና) ነይ ነይ (ና ና) ነይ ነይ (ና ና)
ነይ ነ-ይ



Writer(s): Rophnan


Rophnan - Reflection
Album Reflection
date de sortie
17-05-2018




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.