Sami Dan - Eyangelatagn Newe paroles de chanson

paroles de chanson Eyangelatagn Newe - Sami Dan



Sami Dan
Andy Bete Zema
መሬት የማይነካኝ አየር ላይ ነጣሪ
ሽቅርቅር አማላይ ነገር አሳማሪ
ከኔ በላይ ማነው ብዬ ምፎክር
ነበርኩ እኔ ላገር ማስቸግር
ወይ ጊዜ ወይ እጣ ክፉ ቢገጥመንም
ፍቅር ጠልፎ ጥሎን ከቤት አዋለኝ
ትቢቴን አንጥፎ ከመሬት የጣለኝ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
ከጠዋት እስክ ማታ (እያንገላታኝ ነው)
ሆነሽ ሁሉም ቦታ (እያንገላታኝ ነው)
እኔስ ምን ላርግልሽ ውዴ የኔ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
የኔ እንዲያ መገንፈል አገር ማጥለቅለቁ
አውቀው አሳለፉኝ ቀን እየጠበቁ
በጉልበት ላይ ጉልበት ሲመጣ ድንገት
ያስጨንቃል ያስብላል ወዴት
በሰከነ መንፈስ በረጋው ቃልሽ
ስታነጋግሪኝ ኩራቴን ጥሰሽ
ስንት ርቀት ሄደሽ ነካካሺኝ ድንገት
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
ከጠዋት እስክ ማታ (እያንገላታኝ ነው)
ሆነሽ ሁሉም ቦታ (እያንገላታኝ ነው)
እኔስ ምን ላርግልሽ ውዴ የኔ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
አቅሜን ያጣው ሰው ነኝ
አቅሜን አጣሁኝ ዛሬ
አንገቴን እያስደፋኝ
ባንቺ ሰው መቸገሬ
አንቺ እንደኔ አይደለሽ
እንደኔማ አይደለሽ
ድረሺልኝ በሞቴ
ነይ ባክሽ ቶሎ ብለሽ
ምን ዕዳ ነው ይሉኛል
ምን ዕዳ ነው ይሉኛል ሁሉም
ፍቅር የነካው ሰው
ፍቅር ነው ሚወጣው ቃሉ
አንቺን ምክንያት አርጎ
ፍቅርማ እኔን ካዳነ
ሁሉን ሁሉ ይቀበል
ልቤም ይሁን የታመነ
ከጠዋት እስክ ማታ (እያንገላታኝ ነው)
ሆነሽ ሁሉም ቦታ (እያንገላታኝ ነው)
እኔስ ምን ላርግልሽ ውዴ የኔ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
እያንገላታኝ ነው
ከጠዋት እስክ ማታ (እያንገላታኝ ነው)
ሆነሽ ሁሉም ቦታ (እያንገላታኝ ነው)
እኔስ ምን ላርግልሽ ውዴ የኔ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው



Writer(s): Sami Dan


Sami Dan - Sibet
Album Sibet
date de sortie
01-09-2021




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.