Teddy Afro - Musica Hiwote paroles de chanson

paroles de chanson Musica Hiwote - Teddy Afro



ተው ልጄ ኪነት
ከሀሁ ታረቅ
ተው ልጄ ኪነት
ከሀሁ ታረቅ
በአንቺሆዬ ቃና
የዎራ ሰመሌ
በትዝታ ቃና
በጢና ባሳቦ
በአንቺሆዬ ቃና
ደፊ መስጓላይ ጓላይ
ጓላይ
ደፊ መስጓላይ ጓላይ
ጓላይ
ደርብ!
ሶሌ ሶሌ ያሚጊ ራቃሪ ፈያ
ወላይታ ካኣ
ሙዚቃ ህይወቴ
ግዕዝና እዝል
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ያሬዳዊ ስልት የሰማይ ፀጋ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
አቆራኘኋት ነፍሴን ካንቺ ጋር
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
በሀገሬ ቅኝት የብሄር ቋንቋ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
እደሰታለሁ እኔ አላዝንም በቃ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
በአፋር ሲዳማ በጋምቤላ ቶም
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ልቅጥ ዳንኪራ እኔ አላዝንም ከቶም
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
መሀያ በያባ መሀያ በያባ
ሀያ ባያ መሀያ በያባ
መሀያ በያባ መሀያ በያባ
ሀያ ብዬ እኔ ስለ አብዬ
ሙዚቃ ህይወቴ
ግዕዝና እዝል
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ተው ቢል አልሰማው በልጅነቴ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ገርፎ ሲቀጣኝ ሲመክረኝ አባቴ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ስንት ያየሁብሽ ሙዚቃ ህይወቴ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ቆመህ ካላየህ አታምንምና
ላባብልህ ዛሬ በክራሬ ቃና
በሟች ማዘን የለም
ባለው መፅናናት ነው
ብለህ እንዳስተማርከኝ
ባንተው ምክር ሄጄ
ባንተው አስጨከንከኝ
እርሱ እንዳለው ሎሬቱ
ሞትም ይሙት የታባቱ
በሞትክ ላይ
ፎክሬበት በዳንኪራ
ትነሳለህ ከኔ ጋራ
ትነሳለህ ከኔ ጋራ
መሀያ በያባ መሀያ በያባ
ሀያ ብዬ አልሞትክም አብዬ
መሀያ በያባ መሀያ በያባ
ሀያ ብዬ እኔ አለሁ አብዬ
ሙዚቃ ህይወቴ
ግዕዝና እዝል
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
በዚህ ኑር ብሎ ከላይ ካዘዘ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ልጁ ምን ያድርግ ክራሩን ያዘ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
አትዘንበት አደራ እንግዲ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
ማርኮት ቅኝቱ ምን ያድርግ ቴዲ
አራራይ አራራይ
የተሰጠች ከላይ
መሀያ በያባ መሀያ በያባ
ሀያ ባያ መሀያ በያባ
መሀያ በያባ መሀያ በያባ
ሀያ ብዬ ጀነቱን ለአብዬ



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Arifzefen Singles Collection, Vol. I
Album Arifzefen Singles Collection, Vol. I
date de sortie
28-02-2014




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.