The Christians feat. Hana Tekle - Selam New (feat. Hana Tekle) paroles de chanson

paroles de chanson Selam New (feat. Hana Tekle) - The Christians feat. Hana Tekle



መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ
የአባቶቼ የነ ሙሴ ኣባት
እንደ እግዚኣብሔር ያለ ማንም የለም
የሚያውቅልኝ እንደ አንተ አላገኝም
ብታድነኝም ባታዳነኝም አንተ መልካም ነህ
ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ
ላደረራግህ ማስተካከያ ከማንም ኣትሻም
ፍፁም በስራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም
ያስጨነቀኝ ቀንበሬን ውስጤን አንቆ የያዘው
ለእኔ እንጂ ቢከብደኝ ኢየሱሴ ለአንተ እንዴት እንዴት ቀላል ነው
የዛሬው ድቅድቅ ሌሊቴ ይገባሃል ሚስጥሩ
ፊትህን አያየሁ ዛሬ ግን አላለሁ ሰላም ነው
አዝ፦ ሰላም ነው እላለሁ በእጅህ የገባውን ነገሬን እያየሁ
ሰላም ነው እላለሁ ውስጤ ሸክም አዝሎ እጅህን አያየሁ
አልገባሽ ቢለኝ ነገሩ ማዕበሉን ወጀቡን ፈርቼ
ውስጤ ብርዱ ተሰማኝ ሰው ነኝና ሰግቼ
ጉልበቴ እልሃለሁ ዛሬ አቅሜ አንተ ነህ አቤቱ
እምነቴ እንደው አልታመነም
አይተኸኛል በብዙ ግን እላለሁ
አዝ፦ ሰላም ነው እላለሁ ያደረክልኝ ትናንትን እያየሁ
ሰላም ነው እላለሁ በዚህ ኣይቀጥልም ክብርህን አያለሁ
ሰላም ነው እላለሁ ያደረክልኝ ትናንትን እያየሁ
ሰላም ነው እላለሁ ይህም ሌሊት ያልፋል ክብርህን አያለሁ
ደህና ነው ካለች ሱንማይቷ
የአንድ ልጇን ነፍስ ኣጥታ ከቤቷ
ታድያ እንዴት አልል ሰላም ነው
ባለቤት አለኝ የኔ አይደለሁም
በትንሽ ትልቁ ብዙ ጭንቀቴ
መልስ እንዳይሆነኝ ለዘመመው ቤቴ
ተረድቻለሁ ይህንን አውቄአለሁ
ነገሬን ሁሉ አስረክቤዋለሁ
መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ
ያባቶቼ የነ ሙሴ ኣባት
እንደ እግዚኣብሔር ያለ ማንም የለም
የሚያውቅልኝ አንደአንተ አላገኝም
ብታድነኝም ባታዳነኝም አንተ መልካም ነህ
ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ
ላደረራግህ ማስተካከያ ከማንም ኣትሻም
ፍፁም በሥራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም
ሰላም ነው (፬x)
ሰላም ነው (፬x)
አውጃለሁ ዛሬም መልካምንትህን ባልሞላው ነገሬ
ስንፍና አልሰብክም ዕምነቴን አልጥልም ከንቱ ተናገሬ
ከአንተ በላይ ለእኔ ለመጪው ዘመኔ እኔ አላውቅምና
መቆዘሜን ጥዬ ይህም ያልፋል ብዬ ልለፍ በምሥጋና
ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ሕይወቴ
እንድማር ነው አባቴ
ነፋሱ ሲያይል ሲበረታ
ድንቅህን ላይ ነው የማታ የማታ (፪x)
ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ህይወቴ
ለትምህርቴ ነው አባቴ
ወጀቡ ቢያይል ቢበረታ
ግን ድሉ የእኔ ነው የማታ የማታ (፪x)



Writer(s): Simone Tsegay


The Christians feat. Hana Tekle - Ethiopian Protestant Mezmur, Vol. 2
Album Ethiopian Protestant Mezmur, Vol. 2
date de sortie
17-02-2016



Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.