Текст песни




ሶስት ሁለት ሶስት አንድ ሁለት
ከሸራው ከቡሩሹ መሀል
ውበት ገኖ ይጮሀል
የሰዓሊው ጥበብ ያንቺ መልክ
ለልቤ ሀሴት ሆኗል
አውቃለሁ ብዙ አይቻለው
ምስለ መልካም ብዙ ነው
ለልቤ የተቃኘ ውበት ያንቺ በልኬ ነው
ተመኘው ሰዓሊሽ ቢሸልመኝ ብዬ
አንቺን ቢልሽ ለእኔ
ላኖርሽ ከቤቴ እስከ ሕይወት ዘላለሜ
ሌላ ምስል ሳይኖር ባንቺ መልክ ብቻ
ያጌጥ ነበር ቤቴ
ለአይኔም ሌላ አልፈልግ
ባንቺ ይሰክናል ሕይወቴ
ውብ የእጁ ጥበብ ጌጥ ለአለም
ከውስጥ የወለደሽ ሰዓሊው ከቀለም
ውብ የእጁ ጥበብ እንድታውቂው
ያንቺ መሆን ይሻል ልቤን ስሚው
ከሰጠኝ ሰዓሊው
ከሰጠኝ ሰዓላው
አንቺን ይሁንልህ ብሎ የልቤን ካረገልኝ
አንቺን
ደስታዬ ሙሉ ነው ለቀረው ግድም የለኝ
ቀኑ እንኳን ባይሞላ መስከረም ባይጠባ አዲስ ዓመት
አዲስ አዲስ ዓመት ገባ ለኔ ሕይወት
መልክሽ ለዓይኔ አደይ
ፍቅርሽ ተስፋ ፀደይ የሞላበት
አዲስ አዲስ ዓመት ሆነ ለኔ ሕይወት
ቸር ነው ሳውቀው ሰዓሊሽ
ይኼን ውበት የሸለመሽ
አንድ ያድርገን ይስጠኝና
ወይ ካጠገብሽ ይሳለኝና
ውብ የእጁ ጥበብ ጌጥ ለአለም
ከውስጥ የወለደሽ ሰዓሊው ከቀለም
ውብ የእጁ ጥበብ እንድታውቂው
ያንቺ መሆን ይሻል ልቤን ስሚው
ከሰጠኝ ሰዓሊው
አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ አጀብ
ኦሆዬ



Авторы: Rophnan, Rophnan Nuri Muzeyin



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка