Текст песни




በዚህ አለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ
ባንተ ዘንድ ያለ የሕይወት ቃል ሌላ ስፍራ የትም ማላገኘው
ብርም አይሰጠኝ ወርቅም አይሰጠኝም የሕይወቴን አቅጣጫ የለወጠው
የሁልጊዜ ነው የልቤ ሰላም ከመንፈስህ ከቃልህ የመነጨ
በዚህ አለም ነገር የማይወሰን የኔን ሕይወት የደስታ ያደረገው
ብዙ ደስታ አለ በሕይወቴ ብዙ ደስታ አለ
ብዙ ሰላም አለ በሕይወቴ ብዙ ሰላም አለ
ጌታ ኢየሱስ ከኔ ጋር ስላለህ
መንፈስ ቅዱስ በኔ ውስጥ ስላለህ
ጌታ ኢየሱስ ከኔ ጋር ስላለህ
መንፈስ ቅዱስ በኔ ውስጥ ስላለህ
ሸክም የከበደው ወደ እኔ ይምጣ ይረፍ ብለህ የጠራኸኝ አንተ እኮ ነህ
ሁሉንም ነገር ላንተ ሰጥቼ እፎይ ብዬ ተደላድዬ የምኖርበት
ኢየሱስ ካንተ ጋር ያለኝ ሕብረት ማለት ለኔ አለሜ ነው አለሜ ነው
ለሕይወቴ ትርጉም ያገኘሁበት ምክንያቱ ነው የዘላለሜ የሰመረበት
በዚህ አለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ካንተ ጋር እንዳለሁ
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ




Samuel Negussie - Be'egziaber Alem, Vol. 1
Альбом Be'egziaber Alem, Vol. 1
дата релиза
24-05-2017




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка