Teddy Afro - Chewatash текст песни

Текст песни Chewatash - Teddy Afro



ጨዋታሸ አልጥም አለኝ ዛሬ አነጋገርሽ
ከወትሮው ተለየብኝ ምነው ጭር አለ ፊትሽ
ምናልባት አስቤ ይሆናል ከፍቷት ይሆን ብዬ
ታዲያ እንዴት የሌለሽን አመል ዝም ልበል ችዬ
ዝም ልበል ችዬ
እንደተከፋ ሰው እንዳጣ ሰው ጤና
ክፉ ሲገኝ ካፍሸ ምን ነካሸ አልኩና
ጆሮዬን ለማመን ስላቃተኝ እኔ
አልሄድም ክጎንሽ አትራቂ ከጎኔ
ተይ አታስጨንቂው ልቤን ሲከፋሽ አይወድም
ካልነገርሽኝ ቁርጡን ዛሬ ከጎንሽ አለሄድም
ካንደበትሽ ክፉ ማይወጣሽ
ምን ተገኘ ዛሬ ምን ነካሽ
ጨዋታሸ አልጥም አለኝ ዛሬ አነጋገርሽ
ከወትሮው ተለየብኝ ምነው ጭር አለ ፊትሽ
ምናልባት አስቤ ይሆናል ከፍቷት ይሆን ብዬ
ታዲያ እንዴት የሌለሽን አመል ዝም ልበል ችዬ
ኪዳን አለኝና እስካለም ዘመኔ
ሳቅሽ የኔ ሊሆን ሀዘንሽ ሃዘኔ
ልካፈለውና ያገኘሽን ነገር
ይረፍልኝ ልቤ ጨንቆት ከሚቸገር
ተይ አታስጨንቂው ልቤን ሲከፋሽ አይወድም
ካልነገርሽኝ ቁርጡን ዛሬ ከጎንሽ አልሄድም
ካንደበትሽ ክፉ ማይወጣሽ
ምን ተገኘ ዛሬ ምን ነካሽ



Авторы: Teddy Afro


Teddy Afro - Tikur Sew
Альбом Tikur Sew
дата релиза
01-04-2012




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.