Gigi - Mengedegna Lyrics

Lyrics Mengedegna - Gigi



ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴ አንዴት ብዬ ልተው
ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴ አንዴት ብዬ ልተው
ሆይ ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው ብነግረው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ሆይ ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው ብነግረው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ዪኢኢኢሻለው ነበረ መውደድ ከተራራው
ጥሎ ከማይሄደው ከማይሸሸው ጋራ
ይኢኢኢ ሻለው ነበረ መውደድ ከተራራው
ጥሎ ከማይሄደው ከማይሸሸው ጋራ
ተራራዉ ሰው ሆኖ ከንፈሬን ባይስመኝ
ተራራዉ ሰው ሆኖ ጡቴን ባይዳብሠው
ተራራዉ ሰው ሆኖ አይን አይኑን ባላይ
ጸሀይ እሞቃለሁ ወጥቼ ከላይ
ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴ አንዴት ብዬ ልተው
ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴ አንዴት ብዬ
ልተው
ሆይ ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው ብነግረው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ሆይ ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው ብነግረው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ጎዳናው እእእ መንገዱ
ሼሽቶኛል ስልህ አርቆ ወስዶኛል
ደሞ አዙሮ አዙሮ ካንተ ያመጣኛል
ተዉ ልቤ ተዉ ልቤ ተው ልቤ ተመከር
እምበጅህ ወዳጅ የሚሻል
የሽንብራ ቆሎ እንዴት ጣፋጭ ነው
ቆንጥሬ በልቼ ምኑን ልዋጠው
አንት መንገደኛ አንት መንገደኛ አንተ አደገኛ
አትመጣልኝም ሆይ
አንተን ካላየሁ እንቅልፍም አልተኛም
ሁሁ አንት መንገደኛ አንተ አደገኛ አትመጣልኝም ወይ አንተን ካላየሁ እንቅልፍም አልተኛም
የሽንብራ ቆሎ እንዴት ጣፋጭ ነው ቆንጥሬ በልቼ ምኑን ልዋጠው
አሞራ ወድጄ አሞራ ሆኛለሁ በየትነኛው መንገድ ባልፍ አገኝሀለው
አሀሀሀ መንገደኛ አንተ አደገኛ አትመጣልኝም ወይ አንተን ካላየሁ እንቅልፍም አልተኛ
ሁሁሁ መንገደኛ አንተ አደገኛ አትመጣልኝም
ወይ አንተን ካላየሁ እንቅልፍም አልተኛ



Writer(s): Shibabaw Ejigayehu


Gigi - Gigi
Album Gigi
date of release
28-04-2003




Attention! Feel free to leave feedback.