Yosef Kassa - Yemedane Neger Lyrics

Lyrics Yemedane Neger - Yosef Kassa



ደግሜ ደግሜ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር
አሁንም መልሼ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር
ደግሜ ደግሜ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር
አሁንም መልሼ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር
ቀሎ ስለመጣ አይቀልም በሕይወቴ የመስቀሉ ሥራ
በክብር ታጅቦ ይመጣል ሊወስደኝ አርጎኛል ሙሽራ
ሰማይ ደስታ ሆነ እልልታው ቀለጠ በእኔ መዳን
እንዴት መታደል ነው በበጉ ዙፋን ፊት ከእርሱ ጋር መሆን
አጋንንት ቢወጣ ሽባ ቢተረተር
የሞተ ቢነሳ ይህም ያልፋል ምድር
አይወዳደርም ይህኛው ተአምር
የመዳኔ ነገር(×8)
ደግሜ ደግሜ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር
አሁንም መልሼ ብደጋግም
የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምር
የመዳኔ ነገር(×4)
አማኝ ሞት አይፈራም እንግዳ ነውና በዚህ ምድር ላይ
ይናፍቃል እንጂ ከአምላኩ ጋር መኖር በላይ በሰማይ
ሰው አለምን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል መቼ ይጠቅመዋል
ከክርስቶስ ጋራ ለዘላለም መኖር ከሁሉም ይበልጣል
ጠላቴ ሆይ ስማ ሞኝን አስፈራራ
ሞት አይፈራም አማኝ ሰማይ የሱ ስፍራ
ይሄ አለኝ ብዬ ቁሳቁስ አልቆጥር
የኔ ሀብት ይሄ ነው ሞትን የሚሻገር
የመዳኔ ነገር(×8)
ክብር ቢሆን ያልፋል
ዝና ቢሆን ያልፋል
ውበት ቢሆን ያልፋል
ሃዘን ቢሆን ያልፋል
ማግኘት ቢሆን ያልፋል
ማጣት ቢሆን ያልፋል
የማያልፈው አንድ ነገር
በሰማያት ያለ ክብር
ተጽፎልኝ ስሜ በላይ
ከዚህ በላይ ደስታ አለ ወይ
ለዚህ ነው የኔ ደስታ
ሞልቶኛል እልልታ
ለዚህ ነው ጩኸቴ
ሰማይ ቤት በመግባቴ
ክብር ቢሆን ያልፋል
ዝና ቢሆን ያልፋል
ውበት ቢሆን ያልፋል
ሃዘን ቢሆን ያልፋል
ማግኘት ቢሆን ያልፋል
ማጣት ቢሆን ያልፋል
የማያልፈው አንድ ነገር
በሰማያት ያለ ክብር
ተጽፎልኝ ስሜ በላይ
ከዚህ በላይ ደስታ አለ ወይ
ለዚህ ነው የኔ ደስታ
ሞልቶኛል እልልታ
ለዚህ ነው ጩኸቴ
ሰማይ ቤት በመግባቴ
ለዚህ ነው የኔ ደስታ
ሞልቶኛል እልልታ
ለዚህ ነው ጩኸቴ
ሰማይ ቤት በመግባቴ



Writer(s): Samuel Alemu, Yosef Kassa Unknown


Yosef Kassa - Zmtaw
Album Zmtaw
date of release
02-02-2018




Attention! Feel free to leave feedback.