Yosef Kassa - Teregagtual Lyrics

Lyrics Teregagtual - Yosef Kassa



አንዴ በፍቅሩ ልቤ ተነክቶ
ሌላውን ናቀው በኢየሱስ ረክቶ
በነገረኝ ቃል በእርሱ ጸንቼ
ዘና ብያለሁ ጌታን ሰምቼ
ተረጋግቷል ልቤ ተረጋግቷል
ተረጋግቷል ልቤ ተረጋግቷል
በአምላኩ ታምኖ እፎይ አለ
ከአንተ ድምጽ ውጪ አልሰማ አለ
ኢየሱስን ይዞ ቃሉን ተመርኩዞ
በትከሻው መሃል ተንተርሶ
ኢየሱስን ይዞ ቃሉን ተመርኩዞ
በትከሻው መሃል ተንተርሶ
ልቤም አይፈራም ሁኔታን አይቶ
አይደነብርም ጠላቱን ሰምቶ
እነድ አንበሳ ነው ውስጠ ድፍረቴ
አንዴ አትርፌያለሁ በማንነቴ
በውይኑ ሃረግ ፍሬ ባይገኝ
ቢሆንም ባይሆን አያስጨንቀኝ
ደስ ይለኛል በጌታ ደስ ይለኛል
ዓይናወጥም ከቶ እምነቴ
የሰላም አምላክ ገብቷል ከቤቴ
ደስ ይለኛል በጌታ ደስ ይለኛል
ይህን ነው እንጂ ጀግና ሚሉት
አይደነብርም በሚነግሩት
በሰልፍ መሃል በምጥ ተይዞ
ይደረድራል በገናን ይዞ
ክበር እያለ ንገሥ እያለ
ክበር እያለ ንገሥ እያለ
ተረጋግቷል ልቤ ተረጋግቷል
ተረጋግቷል ልቤ ተረጋግቷል
በአምላኩ ታምኖ እፎይ አለ
ከአንተ ድምጽ ውጪ አልሰማ አለ
ኢየሱስን ይዞ ቃሉን ተመርኩዞ
በትከሻው መሃል ተንተርሶ
ኢየሱስን ይዞ ቃሉን ተመርኩዞ
በትከሻው መሃል ተንተርሶ
ጠላት ሁኔታን እያሳየኝ
ልቤ እንዲከፋ ሲጠብቀኝ
ይናፍቀዋል እንባ ከዓይኖቼ
ምሥጋና ሞልቷል ከከንፈሮቼ
በውይኑ ሃረግ ፍሬ ባይገኝ
ቢሆንም ባይሆን አያስጨንቀኝ
ደስ ይለኛል በጌታ ደስ ይለኛል
ዓይናወጥም ከቶ እምነቴ
የሰላም አምላክ ገብቷል ከቤቴ
ደስ ይለኛል በጌታ ደስ ይለኛል
ይህን ነው እንጂ ጀግና ሚሉት
አይደነብርም በሚነግሩት
በሰልፍ መሃል በምጥ ተይዞ
ይደረድራል በገናን ይዞ
ክበር እያለ ንገሥ እያለ
ክበር እያለ ንገሥ እያለ
የእምነት አባቶቼ እንዲህ መከሩኝ
ሁል ጊዜ በጌታ ተደሰት አሉኝ
ውህኒ ቢከቷቸው የማይመች ቦታ
መዘመር ቀጠሉ ውስጣቸው ነው ደስታ
ቢሆንም ባይሆን አመስግኑ
መልካም እንዲሆን አመስግኑ
ዕልል በሉ አመስግኑ
ዕልል በሉ እንጂ አመስግኑ
አታጉረምርሙ አመስግኑ
አምላክ አትሙ አመስግኑ
ዕልል በሉ ፡፡ አመስግኑ
ዕልል በሉ እንጂ አመስግኑ
ቅዱሳን ሁሉ
ለእርሱ ዘምሩ
አንሱ በገና
አምጡ ምሥጋና
ቢሆንም ባይሆን አመስግኑ
መልካም እንዲሆን አመስግኑ
ዕልል በሉ አመስግኑ
ዕልል በሉ እንጂ አመስግኑ
አታጉረምርሙ አመስግኑ
አምላክ አትሙ አመስግኑ
ዕልል በሉ ፡፡ አመስግኑ
ዕልል በሉ እንጂ አመስግኑ
ቢሆንም ባይሆን አመስግኑ
መልካም እንዲሆን አመስግኑ
ዕልል በሉ አመስግኑ
ዕልል በሉ እንጂ አመስግኑ
አታጉረምርሙ አመስግኑ
አምላክ አትሙ አመስግኑ
ዕልል በሉ ፡፡ አመስግኑ
ዕልል በሉ እንጂ አመስግኑ



Writer(s): Samuel Alemu, Yosef Kassa Unknown


Yosef Kassa - Zmtaw
Album Zmtaw
date of release
02-02-2018




Attention! Feel free to leave feedback.