Yosef Kassa - Yihe New Yegebagn Lyrics

Lyrics Yihe New Yegebagn - Yosef Kassa



ውሰድልኝ ዛሬም ከነፍሴ የሆነ አምልኮዬን
አላገናኘውም ከሁኔታ ጋራ ዝማሬዬን
ትላንት አመስግኜ ዛሬ አላማህም እንዲህ ብዬ
ይጨምራል እንጂ አላሳንሰውም ምስጋናዬን
የማየው ነገር ከምስጋናዬ አያግደኝም
የምሰማው አንተን ከማምለክ አያስቆመኝም
ምድረ በዳዬን አለምልሞታል እያየ ዐይኔ
ባሕሩን ከፍሎ ያሻግረኛል አምናለሁ እኔ
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ውሰድልኝ ዛሬም ከነፍሴ የሆነ አምልኮዬን
አላገናኘውም ከሁኔታ ጋራ ዝማሬዬን
ትላንት አመስግኜ ዛሬ አላማህም እንዲህ ብዬ
ይጨምራል እንጂ አላሳንሰውም ምስጋናዬን
የለመንኩትን የጠየኩትን ጥያቄ ሁሉ
ከምስጋና ጋር እጠብቃለሁ አምኜ ቃሉን
የከበደኝን ሸክሜን ሁሉ በሱ ላይ ጥዬ
በአንዳች ነገር አልጨነቅም አለ ጌታዬ
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ደመና የለም አይታየኝም በዐይኔ
ነፋስም የለም አይታየኝም በዐይኔ
ሳላይ አምናለሁ እንዲህ ይሆናል
ባዶ ሸለቆ ውሃ ይሞላል
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ደመና የለም አይታየኝም በዐይኔ
ነፋስም የለም አይታየኝም በዐይኔ
ሳላይ አምናለሁ እንዲህ ይሆናል
ባዶ ሸለቆ ውሃ ይሞላል
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር
ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር
ምስክር ነኝ እኔ(×2)
አይቻለሁኝ ሲሰራ
ምስክር ነኝ እኔ(×2)
ክንደ ብርቱ ነው ኃይለኛ
ምስክር ነኝ እኔ(×2)
ድንቅ ነው ተአምረኛ
ምስክር ነኝ እኔ(×2)
አይቻለሁኝ በዐይኔ
ምስክር ነኝ እኔ(×6)



Writer(s): Samuel Alemu, Yosef Kassa


Yosef Kassa - Zmtaw
Album Zmtaw
date of release
02-02-2018




Attention! Feel free to leave feedback.