Gossaye Tesfaye - Teregagash Woy paroles de chanson

paroles de chanson Teregagash Woy - Gossaye Tesfaye



በፍቅር የማትረጋ ሰው ወድጄ
ላልይዛት ላላስቀራት አሳድጄ
ይኸው ስከተላት እኖራለሁ
ጨክኜ እንዳልተዋት ጥሎብኝ ደግሞ እወዳታለሁ
ንገሪኝ ኧረ እንደምን ከርመሽ ይሆን
ከማን ጋር ውለሽ አደርሽ ይኼን ሰሞን
ማነው ባለሳምንት ተረኛሽ
ተርጋግቶ ሊኖር እያሰበ እንደኔ ′ሚያጣሽ
ያለቀልብ አቡክተው ያበሰሉት እህል ጠረኑ ቢጠራ
ትርፉ ቃር አይደል ወይ መች ሰውነት ሊሆን የገፉት እንጀራ
ላትኖሪበት ነገር አስር ቤት ለመስራት አስሩን ስታይ
የእግዜሩ እንዳይጠፋሽ መብረሩን አቁመሽ ተረጋጋሽ ወይ?
ተረጋጋሽ ዎይ ተረጋጋሽ ዎይ
ነፍስሽ ከስጋሽ ታረቀልሽ ዎይ
የለበስሺው ልብስ ያጌጥሽው ጌጥ
ለምን ውድ ሆነ ካንቺ ሳይበልጥ
ምን ውድ ቢሆን ይመነችካል
ጨርቃ ጨርቅ ነው በውኃ ያልቃል
ተረጋጋሽ ዎይ ተረጋጋሽ ዎይ
በፍቅር የማትረጋ ሰው ወድጄ
ላልይዛት ላላስቀራት አሳድጄ
ይኸው ስከተላት እኖራለሁ
ጨክኜ እንዳልተዋት ጥሎብኝ ደግሞ እወዳታለሁ
ንገሪኝ ኧረ እንድምን ከርመሽ ይሆን
ከማን ጋር ውለሽ አደርሽ ይኼን ሰሞን
ማነው ባለሳምንት ተረኛሽ
ተረጋግቶ ሊኖር እያሰበ እንደእኔ 'ሚያጣሽ
ለምን አሰራሽው ይኼን ሁሉ ክፍል ይኼን ሁሉ ዋሻ
አራት ክንድ አይደል ወይ የእኔና ያንቺ ቤት በስተመጨረሻ
ለማን አቤት ልትይ ስትሮጪ የታጠቅሺው ስትሮጪ ቢላላ
ውፍረትሽን ንቆ ቢቀጥን እምነትሽ እንደ ማምሻ ጥላ
ተረጋጋሽ ዎይ ተረጋጋሽ ዎይ
ነፍስሽ ከስጋሽ ታረቀልሽ ዎይ
አርጊው በእርጋታ ሁሉን በአቅል
የዘራሽው ነው ነገ ′ሚበቅል
ያበቀለውን የእንባ ጥማድ
ጻዲቅ ብቻ ነው በደስታ 'ሚያጭድ
ጽድቁ ቀርቶብሽ ወጥተሽ ከድጡ
እንዲኮንንሽ እግዜር በቅጡ
በቅጡ ማሰብ ይሁን ስራሽ
ብትኖሪ ከሰው ተረጋግተሽ
ተረጋጋሽ ዎይ ተረጋጋሽ ዎይ
ነፍስሽ ከስጋሽ ታረቀልሽ ዎይ
ኣሄሄሄ ነይ ደሞ ነይ ደሞ



Writer(s): Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Album Siyamish Yamegnal
date de sortie
06-01-2019




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.