Gossaye Tesfaye - Wub Alem paroles de chanson

paroles de chanson Wub Alem - Gossaye Tesfaye



ውብ ዓለም
የሌለሽ እንደው ይጨንቀኛል
ይህ ፍቅርሽ ስንቴ ገድሎ ስንቴ አድኖኛል
ውብ ዓለም
የሌለሽ እንደው ይጨንቀኛል
ይህ ፍቅርሽ ስንቴ ገድሎ ስንቴ አድኖኛል
ስንቴ ገድሎኛል
በድፍረቱ አድቅቆ ቀጥቶኛል
ስንቴ አድኖኛል
በስልጣኑ አፍርሶ ሰርቶኛል
አሀሀሀሀ...
ሰበብ ሆኖ ለሽንፈት ለድሌ
ላጣሁ ላገኘሁት ፍቅርሽ
ኧረ እንዴት ብዬ
ልግለፅሽ አንቺዬ
ህመም መድኃኒቴ ሆነሽ
ንጋቴ ብዬ በፀሐይ መሰልኩሽ
ድካሜ ብዬ ደሞ ስም ሰጠሁሽ
ያለየለት ሆኖ መልከ ብዙ ግራ
ለቃል ቸግሮኛል ምኑን በምን ላውራ
አረገልኝ ብዬ አረገብኝ ባልኩኝ
ስሜን እንደ ዋሾ በሰው አፍ ከተትኩኝ
አዬዬ...
ውብ ዓለም
የሌለሽ እንደው ይጨንቀኛል
ይህ ፍቅርሽ ስንቴ ገድሎ ስንቴ አድኖኛል
ውብ ዓለም
የሌለሽ እንደው ይጨንቀኛል
ይህ ፍቅርሽ ስንቴ ገድሎ ስንቴ አድኖኛል
ስንቴ ገድሎኛል
በድፍረቱ አድቅቆ ቀጥቶኛል
ስንቴ አድኖኛል
በስልጣኑ አፍርሶ ሰርቶኛል
አሀሀሀሀ...
የሆንኩትን ልነግርሽ እልና
ድንገት ይውጠኛል ዝምታ
እኔም ግራ ያጋባኝን ነገር
ላንቺ የምገልፅበት ቃል አጣሁ
ንጋቴ ሆይ የንጋቴ ዝማሬ
ድካሜም አንቺው ለማዝገም ለመዛሌ
ያለየለት ሆኖ መልከ ብዙ ግራ
ለቃል ቸግሮኛል ምኑን በምን ላውራ
አረገልኝ ብዬ አረገብኝ ባልኩኝ
ስሜን እንደ ዋሾ በሰው አፍ ከተትኩኝ
ያለየለት ሆኖ መልከ ብዙ ግራ
ለቃል ቸግሮኛል ምኑን በምን ላውራ
አረገልኝ ብዬ አረገብኝ ባልኩኝ
ስሜን እንደ ዋሾ በሰው አፍ ከተትኩኝ



Writer(s): Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Album Siyamish Yamegnal
date de sortie
06-01-2019




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.