Teddy Afro - Be 70 Dereja paroles de chanson

paroles de chanson Be 70 Dereja - Teddy Afro



ከመኮንን ድልድይ
ከእንጨት ፎቁ በላይ
ሲመሽ እንገናኝ
መጣሁ አንቺን ብዬ
ሳይከብደኝ እርምጃው
በሰባ ደረጃው
(ታም-ታራራም ታራራም ታራራም)
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃው በፒያሳ አድርጌ
በፍቅር ማነቂያው ዶሮ እንዳይል በከንቱ እሪ አንችን ወዶ
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሚያለሁ ከበርሽ ማዶ
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
(ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ)
(አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ)
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
(ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ)
(ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ)
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ)
አምጧት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለ ወጥ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለው
ማነው ካላችሁ ማነው ማነው
ልቤ ልቤ ነው ልቤ ረሃብተኛው
(ልቤ ልቤ ነው ልቤ ረሃብተኛው)
እሷን ወዶ ሌት እማይተኛው
(እሷን ወዶ ሌት እማይተኛው)
ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው
(ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው)
ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው
(ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው)
ዎይ... ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ
ሲመሽ ወደማታ(ሆ) ሁሉ ዘግቶ በሩን(ሆ)
ታም ታራም ሳረገው ብቅ በይ ክራሩን(እይ)
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
ሳረገው ክራሩን
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
ፀጉሯን ተተኩሳው(ሆ) እንዳርምዴ ሜሪ(ሆ)
ዘበናይ ናት ፍቅሯን በክራር ነጋሪ(እይ)
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
በክራር ነጋሪ
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ
ዘማች ሲመለስ
ያወሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምፅ
በክራሩ ድምፅ
ፍቅርሽ አስጨንቆ መላዎስ አቃተኝ
መላዎስ አቃተኝ
ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተኝ
ጥይት እንደሳተኝ
ሳተና ነበርኩኝ ተኳሽ በመውዘሬ
ተኳሽ በመውዘሬ
ለዘበናይ ብቻ እጄን ሰጠሁ ዛሬ
እጄን ሰጠሁ ዛሬ
ዎይ... ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃው በፒያሳ አድርጌ
እንዳውራ ዶሮ ክንፍ ኮቴን እየሳብኩት መሬት ለመሬት
በዞርኩት ገላሽን ሳትወጣብኝ ፀሐይ ሳይነጋብኝ ሌት
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
(ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ)
(አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ)
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
(ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ)
(ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ)
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ) ማታ ማታ
(ማታ ማታ)
ሞልቶ ባራዳ የአርመን ዳቦ
ሳሳ አካላቴ ሰው ተርቦ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለው
ማነው ካላችሁ ማነው ማነው
ልቤ ልቤ ነው ልቤ ረሃብተኛው
(ልቤ ልቤ ነው ልቤ ረሃብተኛው)
እሷን ወዶ ሌት እማይተኛው
(እሷን ወዶ ሌት እማይተኛው)
ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው
(ይውጣ ይውጣ እግሬ ይዛል በርምጃው)
ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው
(ከሷ አይብስም ሰባ ደረጃው)
ዎይ... ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ(ኧረረረ)
አይወጣም ደረጃ(ሆ) ቢፈጥን ሴሼንቶ(ሆ)
እንደኔ ካልሄደ በፍቅር ተገፍቶ(እይ)
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
በፍቅር ተገፍቶ
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
መድፈሪያሽ ወርቅ ነው(ሆ)
ብርም አይገዛሽ(ሆ)
ልብ የሌለው ሐብል ግድም አይሰጥሽ ኬረዳሽ
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
ግድም አይሰጥሽ
ታም-ታራራም ታራራም ታራራም
ከአንገትሽ ላይ አርጊኝ እንደማር ተሬዛ እንደማር ተሬዛ
ወዲህ ወዲያ እንዳልል አደብ እንድገዛ
አደብ እንድገዛ
ተከለከለ አሉ የንጉሥ አዳራሽ
የንጉሥ አዳራሽ
የክት ያለበሰ አይገባም በጭራሽ
አይገባም በጭራሽ
መጣሁ ከኮሪያ ይዤልሽ ሰዓት
ይዤልሽ ሰዓት
በፓሪ ሞድሽ ላይ አምረሽ ታይበት
አምረሽ ታይበት
ዎይ... ዘበናይ ነይ ዘበናይ
ዘበናይ ዘበናይ(አሃ)
ዘብናን እናናዬ(አሃ)
ተይ አሁን ነይ(አሃ)
አሁን ነይ(አሃ)
ዘብናን እናናዬ(አሃ)
ተይ አሁን ነይ(አሃ)
አሁን ነይ(አሃ)
አሁን ነይ(አሃ)
ዘብናን እናናዬ(አሃ)
ተይ አሁን ነይ(አሃ)
አሁን ነይ(አሃ)
አሁን ነይ(አሃ)
ዘብናን እናናዬ(አሃ)
ተይ አሁን ነይ(አሃ)
አሁን ነይ(አሃ)



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Be 70 Dereja
Album Be 70 Dereja
date de sortie
01-10-2015




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.