Gigi - One Ethiopia текст песни

Текст песни One Ethiopia - Gigi



የማንነቴ መለኪያ
ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሦስት ሺህ ዓመት እመቤት
አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ
ሃገሬ እስኪ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል
ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ
ነገሥታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ
ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(እማማ እማማ)
ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ
መድኃኒት አለው የማታ'ማታ
ሀገር በወገን እንዴት ይረታ
ፍቅር በነገር እንዴት ይፈታ
ዘር ሳይለያየን ወይ ሃይማኖት
ከጥንት በፍቅር የኖርንባት
እናት ኢትዮጵያ ውዲት ውዲቷ
በጎጆ አያልቅም ሙሽርነቷ
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(እማማ እማማ)
የማንነቴ መለኪያ
ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሦስት ሺህ ዓመት እመቤት
አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ
ሀገሬ እስኪ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል
ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ
ነገሥታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ
ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(እማማ እማማ)
የማንነቴ መለኪያ
ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሦስት ሺህ ዓመት እመቤት
አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ ማነው የሞሸረሽ
አስጊጦ እንዲ ያሳመረሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል
ሀገሬ አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ
ነገሥታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ
ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(እማማ እማማ)
ሀገር በውበት ወጥመድ ተይዛ
የዘመን ስቃይ ጭንቅ እንደዋዛ
እናት እራቁት እንዴት ልይሽ
ክብርሽ የታለ አንድነትሽ
አርበኛ አርበኛ አርበኛ አላይም
ልውጣ መቅደላ ልበል ዋይ ዋይ
ምነው ቢነሳ መይሳው ካሳ
አልወድም ጎበዝ ጀግና ሲረሳ
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(እማማ እማማ)
(እማማ እማማ)
(እማማ እማማ)
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(ቃል የእምነት እዳ እንጂ ያ'ባት የ'ናት አይደለም)
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
(ቃል የእምነት እዳ እንጂ ያ'ባት የ'ናት አይደለም)



Авторы: Bill Laswell, Ejigayehu Shibabaw


Gigi - One Ethiopia
Альбом One Ethiopia
дата релиза
01-01-1998




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.