Текст песни




የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን
ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር ዓድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር ዓድዋ ትናገር አገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
በኩራት በክብር በደስታ በፍቅር
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን
በቀን በቀን
ደግሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነሱ ለዓድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ ዓድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ
አዪዪ ተናገሪ ተናገሪ
የድል ታሪክሽን አውሪ
አዪዪ ተናገሪ አዪዪ



Авторы: Shibabaw Ejigayehu



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка