Gigi - Bale Washintu текст песни

Текст песни Bale Washintu - Gigi



ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለ ዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሠምቼ ድምፁን
ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለ ዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሠምቼ ድምፁን
ጎንበስ ቀና እያለ አዝመራው ከፊቴ
ቁልቁል ሲወረወር ከማዶ ፏፏቴ
ዋሽንቱን ሲጫወት ልስልስ ባለ ዜማ
ደና ሁን አሠኘኝ ደና ሁን ከተማ
ከግራ ገብሱን ከቀኝ ስንዴውን
አቋርጬ አልፌ ሳየው ሸጋውን
ልቤን እያመሠው የዋሽንቱ ዜማ
ደና ሁን አሠኘኝ ደና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ደና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ተሠነባበተኝ
አሆ እማምዬ ትሠማው የለም ወይ
አሆ እማምዬ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
አሆ አማምዬ አንተ ያገሬ ልጅ
አሆ እማምዬ መዋያህ ከማማ
አሆ እማምዬ ወጣሁ ካንተ ላድር
አሆ እማምዬ ሠለቸኝ ከተማ
ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለ ዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሠምቼ ድምፁን
ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለ ዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሠምቼ ድምፁን
በለመለመው መስክ በወንዙ ዳርቻ
ዋሽንቱን ሲጫወት ሲተክዝ ለብቻ
ከጋራው ላይ ቆሜ ቁልቁል እያየሁት
በሱ ተማርኬ ከተማን ጠላሁት
ከግራ ገብሱን ከቀኝ ስንዴውን
አቋርጬ አልፌ ሳየው ሸጋውን
ልቤን እያመሠው የዋሽንቱ ዜማ
ደና ሁን አሠኘኝ ደና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ደና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ተሠነባበተኝ
አሆ እማምዬ ትሠማው የለም ወይ
አሆ እማምዬ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
አሆ አማምዬ አንተ ያገሬ ልጅ
አሆ እማምዬ መዋያህ ከማማ
አሆ እማምዬ ወጣሁ ካንተ ላድር
አሆ እማምዬ ሠለቸኝ ከተማ
ጎንበስ ቀና እያለ አዝመራው ከፊቴ
ቁልቁል ሲወረወር ከማዶ ፏፏቴ
ዋሽንቱን ሲጫወት ልስልስ ባለ ዜማ
ደና ሁን አሠኘኝ ደና ሁን ከተማ
ያገሬው የወንዜው ሸጋው እረኛ
ኮራ ቀብረር ያለው ጎፈሬው ደገኛ
ከብቶቹን እያየ ሲጫወት ዋሽንቱን
በደስታ ፈዝዤ አየዋለሁ እሱን
አሆ እማምዬ ደና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ተሠነባበተኝ
አሆ እማምዬ ትሠማው የለም ወይ
አሆ እማምዬ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
አሆ አማምዬ አንተ ያገሬ ልጅ
አሆ እማምዬ መዋያህ ከማማ
አሆ እማምዬ ወጣሁ ካንተ ላድር
አሆ እማምዬ ሠለቸኝ ከተማ
እማምዬ
ደና ሁን ከተማ ተሠነባበተኝ
ደና ሁን ደና ሁን ከተማ ተሠነባበተኝ
ትሠማው የለም ወይ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
እማምዬ



Авторы: Shibabaw Ejigayehu


Gigi - Gigi
Альбом Gigi
дата релиза
19-06-2001




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.