Gigi - Semena-Worck текст песни

Текст песни Semena-Worck - Gigi



️ሰምና ወርቅ️
ቅኙት ባለቅኔ ቅኔን ተቀኘው ወርቅን በሰሙ ላይ ደርቦ ጋገረው
ቅኙት ባለቅኔ ቅኔን ተቀኘው ወርቅን በሰሙ ላይ ደራርቦ ጋገረው
እንጀራ ጋጋሪ አዋቄ ሰው ነው
እርሾ የወርቅ ጥሩ ከምን አገኘው
ከወርቅና ከሰም ደራራቦ ጣፈኝ
ልቆ ተጠብቦ በድንቁ ሰራኝ
ቅኔ መርጌታ በቅኔ ይቀኝ
ቅኙት ባለቅኔ ቅኔን ተቀኘው ወርቅን በሰሙ ላይ ደርቦ ጋገረው
ቅኙት ባለቅኔ ቅኔን ተቀኘው ወርቅን በሰሙ ላይ ደራርቦ ጋገረው
ውበት ባለችበት ውበት ትኖራለች
ብርሀን ባለችበት ብርሀን ትኖራለች
ደግነት ባለበት ደግነት ይኖራል
ኑር ብለው ያኖሩት ካኖሩት ይገኛል
ሰው ካለማወቁ ሰውነት ይማራል
ቅኙት ባለቅኔ ቅኔን ተቀኘው ወርቅን በሰሙ ላይ ደርቦ ጋገረው
ቅኙት ባለቅኔ ቅኔን ተቀኘው ወርቅን በሰሙ ላይ ደራርቦ ጋገረው
የደግሰው አፉ ፍኖተ ሰላም በቅን መንገድ ሂዶ ቀኙ ዘላለም
ከፍ ሲሉ ዝቅ ዝቅ ሲሉ ከፍ
ከፍ ሲሉ ዝቅ ዝቅ ሲሉ ከፍ ቁልቁለት ወርጀ ደረስኩኝ ካፋፍ



Авторы: Ejigayehu Shibabaw


Gigi - Gold & Wax
Альбом Gold & Wax
дата релиза
16-05-2006




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.