Jossy Kassa - Altewem Mamesgen текст песни

Текст песни Altewem Mamesgen - Jossy Kassa



አገኘሁኝ ብዬ አልፈነድቅም
አጣሁኝም ብዬ አምልኮ አልተውም
መዳኔ ይበቃኛል ለምሥጋና
የእግዚአብሔር ልጅነት አለኝና
የደህንነቴ ነገር ከሞት መዳኔ
ጌታዬን ለማመስገን በቂ ነው ለእኔ
ጠላቴ ሆይ እፈር እላማርር
ብሞትም ያድነኛል እግዚእብሔር
(አልተውም) ጌታዬን ማመስገን
(አልተውም) ወጀቡ ቢበዛ
(አልተውም) እንደውም ልጨምር
(አልተውም) ምሥጋናዬን ላብዛ
ለእኔ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ)
ሁሌ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ)
አገኘሁኝ ብዬ አልፈነድቅም
አጣሁኝም ብዬ አምልኮ አልተውም
መዳኔ ይበቃኛል ለምሥጋና
የእግዚአብሔር ልጅነት አለኝና
ዛሬ በበረከቱ ቢባርከኝ
የሰጠኝን መልሶ ቢወስድብኝ
እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ
ሥሙ ይባረክልኝ አምልኮ ላብዛ
(አልተውም) ጌታዬን ማመስገን
(አልተውም) ወጀቡ ቢበዛ
(አልተውም) እንደውም ልጨምር
(አልተውም) ምሥጋናዬን ላብዛ
ለእኔ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ)
ሁሌ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ)
በላይ በሰማይ ቤት አለ የሚሉ
ደስ ይበላቸው እልል ይበሉ
ደስታዬ (ነው መዳኔ)
እረፍቴ (ነው መዳኔ)
ሰላሜ (ነው መዳኔ)
መዳኔ (ነው መዳኔ)
በላይ በሰማይ ቤት አለ የሚሉ
ደስ ይበላቸው እልል ይበሉ
ደስታዬ (ነው መዳኔ)
እረፍቴ (ነው መዳኔ)
ሰላሜ (ነው መዳኔ)
መዳኔ (ነው መዳኔ)
ሰላሜ (ነው መዳኔ) መዳኔ (ነው መዳኔ)



Авторы: Simone Tsegay


Jossy Kassa - Teneshina Abrie, Vol. 2
Альбом Teneshina Abrie, Vol. 2
дата релиза
23-11-2010



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.