Jossy Kassa - Tew Belew Enge текст песни

Текст песни Tew Belew Enge - Jossy Kassa



ሰው ሆይ ሰው ሆይ
ሰው ሆይ ሰው ሆይ
ሰው ሆይ (ተው በለው)
ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ ማልዶ
ክፉ ነገር ዘርቶ የወደደውን አደርጎ ሄደ
መልካምና ክፉ ዘር ነበር በእጁ
ጊዜው ደረሰና ዝቅ ብሎ አጨደው አይ መከራ
ምን ይለዋል መልካሙን ቢዘራ
ክፉውን ዘርቶ መጣበት መከራ
አዬ ጉዱ ባያስተውል እርሱ
ጊዜው ደርሶ መጣበት መዘዙ
(የዘራውን አገኘ) ዘርቶ ማጨዱ ግድ ነበረ
(የዘራውን አገኘ) ከዘራው ቦታ መብቀል ጀመረ
(የዘራውን አገኘ) አቤቱ ማረኝ ሲል ተናዘዘ
(የዘራውን አገኘ) ሰማይ ይቅር ቢል ምድር ቂም ያዘ
ስዘራው የሚቀለኝ ሳጭደው የሚከብደኝ
አለማስተዋሌ ጉድ እንዳያረገኝ
እኔም ፈራሁኝ አይ ጉዴ
ክፉ ዘርቶ ማጨዱ ከበደው
ሀዘኑም በረታ አሳመመው
ሲዘራ መች እንደዚህ መሰለው
መከራ አስተማረው
(አስተዋይ ተማረ አስተዋይ)
አሁን እኔም ለራሴ ፈራሁኝ
የምዘራው መልሶ እንዳያንቀኝ
የማደርገውን ሁሉ እንዳስተውል አስተዋይ አርገኝ
(አስተዋይ ተማረ አስተዋይ)
ክፉ ዘርን ሳያስተውል ጥሎ
ተቀመጠ አገር ሰላም ብሎ
ሲቃይ ያዘው ቀን ጠበቀውና
ዘርቶ ማጨድ ተወስኗልና
(የዘራውን አገኘ) ዘርቶ ማጨዱ ግድ ነበረ
(የዘራውን አገኘ) ከዘራው ቦታ መብቀል ጀመረ
(የዘራውን አገኘ) አቤቱ ማረኝ ሲል ተናዘዘ
(የዘራውን አገኘ) ሰማይ ይቅር ቢል ምድር ቂም ያዘ
ስዘራው የሚቀለኝ ሳጭደው የሚከብደኝ
አለማስተዋሌ ጉድ እንዳያረገኝ
እኔም ፈራሁኝ አይ ጉዴ
"በስውር የሚሰራ በግልጽ እንዲከፈለው
ዘርቶ እንደሚታጨድ ማነው የሚያስተውለው
የምን ጉድ መጣብኝ ብለህ እንዳትፈራ
የትላንት ስህተትህ መከራን ሲያፈራ
ጌታማ ምሮኛል ስጋ መች ሊለቀኝ
የዘራሁትን ሁሉ ማጨድ አይቀርልኝ
ሥጋ በሥጋ ሳይቀጣ አይቀርም እንደሚል በቃሉ
ዛሬ ሚዘራው ነገ ይበቅላልና ምከሩ ተው በሉ
በል እንግዲህ አይዞህ አሁንም ጊዜ አለህ
የኋላህን ትተህ የፊትህን እያየህ
መልካም መልካሙን ብቻ ዝራ
ሕይወት እንዳይሆንብህ መከራ"
ክፉ ዘርቶ ማጨዱ ከበደው
ሀዘኑም በረታ አሳመመው
ሲዘራ መች እንደዚህ መሰለው
መከራ አስተማረው
(አስተዋይ ተማረ አስተዋይ)
አሁን እኔም ለራሴ ፈራሁኝ
የምዘራው መልሶ እንዳያንቀኝ
የማደርገውን ሁሉ እንዳስተውል አስተዋይ አርገኝ
(አስተዋይ ተማረ አስተዋይ)
ሰው ሆይ ሰው ሆይ
ሰው ሆይ ሰው ሆይ
ሰው ሆይ (ተው በለው)



Авторы: Simone Tsegay


Jossy Kassa - Teneshina Abrie, Vol. 2
Альбом Teneshina Abrie, Vol. 2
дата релиза
23-11-2010



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.