Meskerem Getu - Tibebin Yemitesete текст песни

Текст песни Tibebin Yemitesete - Meskerem Getu



ጥበብን የሚሰጥ ጥበበኛ
የሕይወት ውኃ ወንዝ የእኔ መገኛ
እግዚአብሔር እርሱ የእኔ ነው
ኧረ ማነው ከእኔ ሚለየው
እግዚአብሔር እርሱ የእኔ ነው
እስቲ ማነው ከእኔ ሚለየው
ልጅ ቢወለድ ከባለጠጋ
ይካፈላል ከአባቱ ጋር
ሃብቱ ሁሉም ቅርሱ የእርሱ ነው
ግን የሚያልፍ ጊዜያዊ ነው
የእኔስ አባት ከሁሉ የላቀ
ሁሉን ገዢ በዓለም የታወቀ
እኮራለሁ ልጁ በመሆኔ
ኤልሻዳይ ነው አባቴ ለእኔ
ኃጢአት አልስራ እንጂ የማያከብረውን
ሌላ ምን ይኖራል እኔና እርሱን ሚለየን
በፀጋው በርትቼ እኖርለታለሁ
እንደ ሚያግዘኝ ጌታን አምነዋለሁ
አባ አባ ብዬ ስለው
አቤት ሚለኝ የቅርቤ ነው
ሚጠብቀኝ እንደ ዓይኑ ብሌን
ማን ሊወስደው ከእኔ ጌታዬን
የእኔስ አባት ከሁሉ የላቀ
ሁሉን ገዢ በዓለም የታወቀ
እኮራለሁ ልጁ በመሆኔ
ኤልሻዳይ ነው አባቴ ለእኔ
ኃጢአት አልስራ እንጂ የማያከብረውን
ሌላ ምን ይኖራል እኔና እርሱን ሚለየን
በፀጋው በርትቼ እኖርለታለሁ
እንደ ሚያግዘኝ ጌታን አምነዋለሁ




Meskerem Getu - Eketelehalehu
Альбом Eketelehalehu
дата релиза
10-09-2014




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.