Meskerem Getu - Hiwoten Fewise текст песни

Текст песни Hiwoten Fewise - Meskerem Getu



ብላቴና ሳለሁ የመረጥከኝ አምላክ
ለአንተ እንድዘምር ታማኝ አርገህ ቆጥረህ
በሁለንተናዬ እንዳከብርህ አንተን
ፀጋህን አብዛልኝ ፈውሰው ሕይወቴን
እባክህ ኢየሱስ እባክህ ኢየሱስ
ሕይወቴን ፈውስ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ስምህ እንዲቀደስ
እባክህ እግዚአብሔር እባክህ እግዚአብሔር
ሕይወቴን ቀይር
ሰዎች እኔን ሲያዩ ስምህ እንዲከበር
እባክህ ባክህ እግዚአብሔር
ሕይወቴን ቀይር
ሕይወቴን ቀይር
እባክህ
ሕዝብህን ልትባርከው ስትሰጠኝ ፀጋ
ከትላንቱ ይልቅ ወደ አንተ ልጠጋ
ለታይታ አይሁን መንፈሳዊነቴ
አንተን እንዲገልጥህ መላው እኔነቴ
ኢየሱስ አባቴ
ኢየሱስ አባቴ
ክበር በሕይወቴ
በሁሉ ይገለጥ የሕይወት እድገቴ
ስለእኔ ኃጢአት ድምህ ፈሶልኛል
እራስህን ሰውተህ ሕያው አድርገከኛል
እኔ ግን ለአንተ መኖር ተስኖኛል
እጅህ ግን ከመጣ አድኖ ያስቀረኛል
እባክህ ኢየሱስ
እባክህ ኢየሱስ
ሕይወቴን ቀድስ
አንተን ለተራቡ ቃልህን እንዳለ
ሕያውና ቅዱስ መሷዕት አድርጌ
ለአንተ ሰውነቴን እንዳቀርብ አምላኬ
በፍፁም መለወጥ ሕይወቴ ይገራ
በዘመኔ ሁሉ አንተን እንድፈራ
እባክህ እግዚአብሔር
እባክህ እግዚአብሔር
ሕይወቴን ቀይር
ደግሞም መጨረሻዬ በፊትህ እንዲያምር




Meskerem Getu - Eketelehalehu
Альбом Eketelehalehu
дата релиза
10-09-2014




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.