Teddy Afro - Selam (Live) текст песни

Текст песни Selam (Live) - Teddy Afro



ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም
አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም
ይህ ዓለም ንዋይ ጭኖ ወርቁን በሙዳይ
ማርኮት ከረታት ነፍሴን ከሰጣት ጉዳይ
ህሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ
ሳይተኙ ማደር ሊሆን ከራስ ተጣልቶ
ከዚህ ሁሉ ቅጣት
ይሻላል ማጣት
አስኮንኛት ነብሴን
አልሞላም ኪሴን
ነብሴ እጅ እንዳትሰጪው ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ያሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን፡ አልሞላውም ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን፡ ባዶ ላርገው ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ይሄን ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም፡ እኔ አላጣም ሰላም
አላጣም ሰላም፡ እኔ አላጣም ሰላም
የአመል ነው እንጂ ደሃ፡ የገንዘብ የለም
ሰው ባይኖር እይዋት እራሷን፡ ባዶ ናት አለም
ገንዘብ ብቻ ነው ያለ፡ የዚህ አለም ደስታ
ዳግም ይሸጣል ስሞ፡ ቢመለስ ጌታ
ለሰላሣ ዲናር
ሊያጣ ነብስ ይማር
አስኮንኛት ነብሴን
አልሞላም ኪሴን
ነብሴ እጅ እንዳትሰጪ ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን፡ አልሞላውም ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን፡ ባዶ ላርገው ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን




Teddy Afro - Ethiopia Wede Fikir (Live)
Альбом Ethiopia Wede Fikir (Live)
дата релиза
29-04-2019




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.