Teddy Afro - Yaseteseral (Live) текст песни

Текст песни Yaseteseral (Live) - Teddy Afro



ያስተሰርያል!
ግርማዊነታቸው ከዚህ ሰረገላ
ወደዋገን ወርደው ሲተኩ በሌላ
በአዛውንቶች እራስ ጉድጓድ ምሳ
አብዮት ሞላችው የተማሪ ሬሳ
ያስተሰርያል!
በ፲፯ መርፌ በጠቀመው ቁምጣ
ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲወጣ
እንደ አምናው ባለቀን ያምናውን ከቀጣ
አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ
ይቅር በለውና የበደለን ወቅሰህ
ምህረት አስተምረን
አንድ አድርገን መልሰህ
ያስተሰርያል!
እማማ ኢትዮጵያ
እማማ አቢሲንያ
እማማ ኢትዮጵያዬ
እማማ ሳባዊ እስራኤል
እማማ ኢትዮጰያ ስሚ!
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ቂም በቀል ክፉ ነው
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ከአምላክ ያለያያል
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ተዋዶ መትጋት ከቅጣት ያስተሰርያል
ኦ... ያስተሰርያል
ጃ!
ያስተሰርያል!
ኤ... ጃ!
ያስተሰርያል!
ዘፀአት ለኢትዮጵያ ወደ ተስፋ ጉዞ
ባህሩን ሚያሻግር አንድ ሙሴ ይዞ
ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጵያ ትንሳኤ
ባንድነት ከገባን የፍቅር ሱባዔ
ያስተሰርያል!
ፍቅር አጥተን እንጂ በረሃብ የተቀጣን
አፈሩ ገራገር ምድሩ መች አሳጣን
ኦሲሳ ኦሲሳ ኦሲሳ ማንዴላ
ይቅር አባብሎ እንዳስጣለ ቢላ
በተስፋዋ መሬት እንዲፈፀም ቃሉ
ሞፈሩን ያዙና ይቅር ተባባሉ
ጃ!
ያስተሰርያል!
እማማ ኢትዮጵያ
እማማ አቢሲንያ
እማማ ኢትዮጵያዬ
እማማ ሳባዊ እስራኤል
እማማ ኢትዮጰያ ስሚ!
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ይሄም በክፋ ቃል
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ይሄንን ሲወቅሰው
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ይሄም በጥላቻ
እማማ አቢሲኒያ
እማማ ይሄንን ሲወቅሰው
እማማ አቢሲኒያ
እማማ መለየት አቃተን የሚበጀንን ሰው
ኦ... ያስተሰርያል
ጃ!...እማማ
እማማ!
እማማ ኤሎሄ ኤሎሄ
እማማ ላማ ሰበቅታኔ
እማማ ኢትዮጵያዬ
እማማ አትሰማኝም ወይ በይ
እማማ እማማዬ
እማማ ማለት ፈጣሪ
እማማ መሰረይ ይቅርታ
እማማ እኛ ስንዋደድ
እማማ ይሰማሻል ጌታ
እማማ ኤሎሄ ኤሎሄ
እማማ እማማዬ
እማማ እስቲ ተዋደዱ
እማማ ይያያዝ እጃችሁ በልዩነታችሁ
እማማ አለበለዚያማ
እማማ በምን ያስታውቃል እኛን መውደዳችሁ
እማማ አቤት ስቃይ አቤት ጠኔ
እማማ ሰማይ ጨክኖ በወገኔ
እማማ ስንት አሳልፈን
እማማ አልቅሰን ሳናባራ ብለን ወይኔ
እማማ እዚጋ ደሞ ሌላ ትኩሳት
እማማ ወገኔ አለቀ በወሲብ እሳት
እማማ እሳት እሳት
እማማ እረ አይነጋም ወይ!
እማማ አይነጋም ወይ
አይነጋም ወይ ሌቱ ኢትዮጵያዬ
እማማ እማማዬ
እማማ ሳባዊ እስራኤል
እማማ እማማዬ!



Авторы: Teddy Afro


Teddy Afro - Ethiopia Wede Fikir (Live)
Альбом Ethiopia Wede Fikir (Live)
дата релиза
29-04-2019




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.