The Christians feat. Hana Tekle - Temesgen текст песни

Текст песни Temesgen - The Christians feat. Hana Tekle




አግዘኝ ደግፈኝ ብዬ ነበረ
የእኔ ጌታ ሰማኸኝ ስለቴም ሰመረ
ብዬ እልሃለው እንደገና
በአዲስ ዝማሬ በአዲስ ዜማ
የአየሁትን በዓይኔ አይቻለሁ
እጅህን በብዙ አይቻለሁ
ምሥጋናዬ በፊትህ ያርግልኝ
አምልኮዬ በፊትህ ይፍሰስልኝ
ዝማሬ በፊትህ ሞገስ ያግኝልኝ
አንተ አይደለህም ወይ ረዳቴ
በጭንቅ ዘመን እረፍቴ
በማያምር ቀን ወበት ድምቀቴ
የደስታዬ ድምጽ ጩኸቴ (፪x)
የለኝም ሌላ እኔ የምለዉ
ይሄ ነው ብዬ እንኳን የማነሳው ከሰው
የድስታዬ ቀኑ ባለቤት
ብቻህን ታይበት ይህን ነው የምለው
ተመሥገን ተመሥገን (፰x)
አዘኑ ክፉ ያዩልኝ ቀኖቼ
እንባን የሻቱ ለዓይኖቼ
ቀኔን አዘኸው ከላይ ከሠማይ
ጠገብኩ በደስታ ሳቅ ሲሳይ (፪x)
የለኝም ሌላ እኔ የምለዉ
ይሄ ነው ብዬ እንኳን የማነሳው ከሰው
የድስታዬ ቀኑ ባለቤት
ብቻህን ታይበት ይህን ነው የምለው
ተመሥገን ተመሥገን (፰x)
ይገባሃል ተመሥገን (፬x)
ተመሥገን (፬x)



Авторы: Samuel Alemu, The Christians Unknown


Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.