Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - One Ethiopia Lyrics

Lyrics One Ethiopia - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የ፫፼ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንች የኔ ሙሽራ ሀገሬ እስቲ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጲያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ
እማማ
ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ
መድሀኒት አለው የማታ ማታ
ሀገር በወገን እንዴት ይረታ
ፍቅር በነገር እንዴት ይፈታ
ዘር ሳይለያየን ወይ ሃይማኖት
ከጥንት በፍቅር የኖርንባት
እናት ኢትዮጵያ ውዲት ውዲቷ
በጎጆ አያልቅም ሙሽርነቷ
እማማ እናት ኢትዮጲያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ
እማማ
የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
፫፼ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ ሀገሬ እስቲ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጲያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ
እማማ
የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
፫፼ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ ማነው የሞሸረሽ አስጊጦ እንዲህ ያሳመረሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ሀገሬ አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁ ነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ ዓለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጲያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ
እማማ
ሀገር በውበት ወጥመድ ተይዛ
የዘመን ስቃይ ጭንቅ እንደዋዛ
እናት እራቆት እንዴት ልይሽ
ክብርሽ የታለ አንድነትሽ
አርበኛ አርበኛ አርበኛ ላይ
ልውጣ መቅደላ ልበል ዋይ! ዋይ!
ምነው ቢነሳ መይሳው ካሳ
አልወድም ጎበዝ ጀግና ሲረሳ
እማማ እናት ኢትዮጲያ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ
እማማ
እማማ
እማማ
እማማ
እማማ
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም
እማማ እናቲቱ
እማማ አንቺ እናት ዓለም



Writer(s): Bill Laswell, Ejigayehu Shibabaw, Bill O Laswell


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - One Ethiopia




Attention! Feel free to leave feedback.