Meskerem Getu - Yene Neger Lyrics

Lyrics Yene Neger - Meskerem Getu




አዝ፦ የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይ
የያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ
ማደሪያው ልግባና
ላምልከው አንስቼ በገና
የማማርረው አልሞላም ብዬ
ስሙን ላወድስ ሀዘኔን ጥዬ
ቢጐድልም እንኳን ወይኑ በለሱ
በዚህ አይለካም ጌታ ነው እርሱ
ጌታ ነው ጌታ
ላመስግነው ሳለይ ሁኔታ
እኔ አለሁኝ አለሁኝ አበዛለው ብዙ ምስጋና
ሰው ሆኛለሁ ጌታዬ ኢየሱሴ በሰራው ስራ
ከትላንቱ ከአስፈሪው ከጨለማው ከዚያ ግዛት
ያመለጠ የዳነ ለጌታዬ ይስገድለት
አምጡለታ አምጡለታ
ሲያንስበት ነው እልልታ ለዚህ ጌታ
አዝ፦ የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይ
የያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ
ማደሪያው ልግባና
ላምልከው አንስቼ በገና
የዘላለም አባት የመዳኛ ደግሞም ካህኔ
እጅግ ብዙ ብዙ ነው አምለኬ የሆነው ለእኔ
ከአባቱ ቀኝ ሆኖ ስለእኔ እየማለደ
ዛሬም አለው በእቅፉ ጠላቴን እያዋረደ
አምጡለታ አምጡለታ
ሲያንስበት ነው እልልታ ለዚህ ጌታ
አዝ፦ የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይ
የያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ
ማደሪያው ልግባና
ላምልከው አንስቼ በገና





Attention! Feel free to leave feedback.