Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Kahn paroles de chanson

paroles de chanson Kahn - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



በቃላት ድርድር በሙዚቃ ቃና
ስሜት ስታብራራ ነብሴን ስታጣራ
አየሁኝ ጠበብ ሰማሁኝ እዉቀት
ልናገር ልመስክር የዚህን ሰዉ ፅናት
ቀልጦ እንደሚበራ ሻማ
መብራት በሌለዉ ከተማ
እየቀለጠ በራልኝ
እየሞተ አኖረኝ
ለሱስ ባለዳዉ ነኝ
ህይወት እንዳይሰለቸኝ
ሲጨነቅ ሲጠበብ
አይተኛም ቀን ከሌት
ለደስታየ ሲዋትት
ካህኔ የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
ካህኔ የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
መሰንቆዉን ይዞ ከደጅ
ሲጫዎት ያድራል ሲያዜም
በበገና በክራር ነብሴን ሲያለመልም
እንደ መልከ ፀዴቅ ካህን
እዉነቱ ከዘመን ዘመን
የዘላለም አይደለም ወይ
የሰጠኝ ደስታ ከላይ
ስወድ ስጠላ የማይተወኝ
ለትንሽ ደስታም አመስጋኝ
እንዲህ ያለሰዉ የሰዉ ምርጥ
በግዜ የማይለወጥ
ካህኔ የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
ቃል ካንደበቱ እንደዉሃ
ይፈሳል እንደ ጅረት
ልብን የሚመረምር
ጠልቆ የሚገባ ካንጀት
ሰምና ወርቁን ተናገር
ቅኔ ደርድር
በፃዲቅ ሰዉ ቃላት
ነብሴ ገባች ከገነት
ጣዕሙን ዜማ ስታዜም
ቃልን ከህይወት ስትቀምም
ስጋየን ለየህ ከነብሴ
አቆራረጥከኝ ከስትንፋሴ
ካህኔ የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
እንደ መልክ ፀዴቅ ካህን
እዉነቱ ከዘመን ዘመን
የዘላለም አይደለም ወይ
የሰጠኝ ደስታ ከላይ
ከላይ ከላይ ከላይ
ከሰማይ
ከላይ ከላይ ከላይ
ከሰማይ



Writer(s): Ejigayehu Shibabaw


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gigi
Album Gigi




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.