Teddy Afro - Emma Zend Yider (Amsale Tobit) paroles de chanson

paroles de chanson Emma Zend Yider (Amsale Tobit) - Teddy Afro



'ማ ዘንድ ይደር ሄዶ ጎኔ
ሰው አልሆንም ካላንቺ እኔ
'ማ ዘብ ኖሮ ለኔ ገላ
ደግሞ አያለሁ ካንቺ ሌላ
ልምጣ ወይ ልቅር ምን ይሻለኛል
ከፍቅርሽ 'ሚያስጥል
ማን ዘንድ ይገኛል
ስለት አለብኝ ከርቤ እና እጣን
ለመተያየት እንዲያበቃን
የጠቢቡ ሰው የሊቁን ቅኔ
ህልሜ አይፈታም ሳላይሽ ባይኔ
'ማ ዘንድ ይደር ሄዶ ጎኔ
ሰው አልሆንም ካላንቺ እኔ
ማ'ዘብ ኖሮ ለኔ ገላ
ደ'ሞ አያለሁ ካንቺ ሌላ
የብራና ስዕል አይነ ጎላዬ
መልከ ማክዳ ሳባ መሳዬ
የሸማሽ ጥለት ቀልሞ ሰንደቄ
ያስታውሰኛል ላንቺ መውደቄ
ልቤ አምሮህ ሌላ ዝቅ አትበል ይቅር
አገር ያህላል ከፍ ያለ ፍቅር
ማ' ዘንግ ይዞ ገብቶ ገዳም
ያገናኘው ፍቅርን ካ'ዳም
ማ' ፆም ይዞ ቆጥሮ ጠጠር
ባሳከለው ፍቅርን ሃገር
ባሳከለው ፍቅርን ሃገር
ባሳከለው ፍቅርን ሃገር
'ማ ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር
'ማ ዘንድ ይደር
ሰው አሳዝኖ ሰው ላይሆን ነገር
ምን አስጀመረዉ የማይሆን ነገር
ልቤ አንቺን ትቶ ከማን ዘንድ ይደር
ልማልልሽ ወይ 'ቶ' መስቀሌ
ከራሴ ጋር ነው ብጣላሽ ጥሌ
ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
ድር አስተርታሪ ጥልፍ የጠለፈው
አስዋብኩሽ ብሎ ምን አስጎበረው
ሸማ ተጊጦ ቀለም ቢነከር
ልብስ አያምርበት ያ'ራቁት ሃገር
ልብስ አያምርበት ያ'ራቁት ሃገር
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር
ልምጣ ወይ ልቅር አጣሁ መንገድ
እግሬ እንዴት ይጥፋው ቆርጦ መሄድ
እይ ሰው ሲወጣ እይ ሰው ሲወርድ
እንዲህ አይደለም ወይ መራመድ
ይህ አይደለም ወይ መራመድ
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Ethiopia
Album Ethiopia
date de sortie
02-05-2017




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.