Abyssinia Infinite - Ethiopia текст песни

Текст песни Ethiopia - Abyssinia Infinite




ጎራው ና()
ሃገሬ ኢትዮጵያ ተራራሽ ማማሩ
እምዬ ኢትዮጵያ ተራራሽ ማማሩ
ወንዙና ጅረቱ ኩሬው ሸንተረሩ()
አይርብ አይጠማውም አይከፋውም ደሜ()
ቢርበኝ እበላለሁ ቀጋውን ለቅሜ
ቢርበኝ እበላለሁ እንኮዩን ለቅሜ
እሾህ እንኮዩን እንጆሪ ለቆሜ
ኢትዮጵያ()
አይክፋሽ እናቴ
ምንም ደሃ ብሆን አለሁ በሕይወቴ
ጎትጉችኝ እስቲ አንቂኝ ከእንቅልፌ
ቤቴን ሳላፀዳ እንዳልቀር ሰንፌ
ቀኔን ሳላሳምር እንዳልቀር ሰንፌ
ሳልስቅ ሳልጫወት እንዳልቀር ሰንፌ
እምዬ እናት ዓለም
እስቲ አንቂኝ ከእንቅልፌ
እምዬ እናት ሃገር
እስቲ አንቂኝ ከእንቅልፌ
ክፉ ገዢ መጣ ደግ ንጉስ መጣ
ሁሉም ይሄዳሉ እንዳመጣጣቸው
ክፉ ንጉስ መጣ ደጉ ንጉስ መጣ
ሁሉም ይሄዳሉ እንዳመጣጣቸው
ሳቅና ለቅሶሽን አይገዙትምና
ሁሉም ይሄዳሉ እንዳመጣጣቸው
ሳቅና ለቅሶሽን አይገዙትምና
አትፍሪ እናት ዓለም ኑሪልኝ በጤና
ኢትዮጵያ()



Авторы: Bill Laswell, Ejigayehu Shibabaw



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.