Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Anten текст песни

Текст песни Anten - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



የማነው ቆንጆ የማን ሸበላ
ባይኖቹ ውበት ልብ የሚበላ
አከናፈሩ የማር ወለላ
ጠይም ቆንጆ ነው የኔ ጎርዳዳ
አለባበሱ አቤት አራዳ
በዚ ልጅ ፍቅር ልቤ ተጎዳ
ምነው ኮራብኝ ተንቀባረረ
ልቤን በመውደድ እያሳረረ
ፍቅርን ደብቆ ፍቅር ያሰተማረ
ልቤ ዘልዓለም ለፍቅርህ ተሰጠ
እንዴት እኖራለሁ መኖር ከዚህ ከበለጠ
ይሄው ሰጠሁህ ያለኝን በሙሉ
አታሳዝነው ልቤን ያላመሉ
ውሰደው ፍቅርህን እጄ ተዘርግቷል
ትላንትናም ዛሬም ልቤ ላንተ ተንበርክኳል
ውሰደው ፍቅርህን እጄ ተዘርግቷል
ትላንትናም ዛሬም ልቤ ላንተ ተንበርክኳል
ክፈትልኝ ልብህን
ግልፅ አርግልኝ ፍቅርህን
ያላንተ ማንም የለኝም
ካንተ ሌላ ሰው አይሆነኝም
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን ተው አትራቅ ወዳጄ
አንተን ደጅ ስጠናህ ወድጄ
አንተን ግባ ቤቴ ውብ ሰው
አታስጨንቀኝ ደግሞ የልቤን ቤት ዛሬም ሰው አነሰው
የማነው ቆንጆ የማን ሸበላ
ባይኖቹ ውበት ልብ የሚበላ
አከናፈሩ የማር ወለላ
ጠይም ቆንጆ ነው የኔ ጎርዳዳ
አለባበሱ አቤት አራዳ
በዚህ ልጅ ፍቅር ልቤ ተጎዳ
ምነው ኮራብኝ ተንቀባረረ
ልቤን በመውደድ እያሳረረ
ፍቅርን ደብቆ ፍቅር ያሰተማረ
ኦይ! ወይ ልቤ ወይ መውደድ
ልክ የለውም ሲወድ
ውሰደው ፍቅርህን እጄ ተዘርግቷል
ትላንትናም ዛሬም ልቤ ላንተ ተንበርክኳል
ውሰደው ፍቅርህን እጄ ተዘርግቷል
ትላንትናም ዛሬም ልቤ ላንተ ተንበርክኳል
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን አንተን እያለ
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን አንተን እያለ
ልቤ ጥሎኝ ኮበለለ
አንተን ተው አትራቅ ወዳጄ
አንተን ደጅ ስጠናህ ወድጄ
አንተን ግባ ቤቴ ውብ ሰው
አታስጨንቀኝ ደግሞ የልቤን ቤት ዛሬም ሰው አነሰው



Авторы: Ejigayehu Shibabaw


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gold & Wax
Альбом Gold & Wax




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.