Gossaye Tesfaye - Wa текст песни

Текст песни Wa - Gossaye Tesfaye



ሰው አይጠፋም ቤትሽ
ከእሁድ እስከ ከእሁድ
ዳስ ጥለሽበታል ላንድም ቀን ላይወርድ
ያላየሽ አይድንም ቀና አይሆንም ቀኑ
የሚል አዋጅ አለ እስኪመስል ሙሉ
አይነጥፍም አይጎድልም ማጀትሽ ቢጠጡ ቢበሉ
እስከ እሁድ ሰው እንዲ መውደድ
እንዴት ብሎ ያንን ሁሉ አባብሎ
ከአንድ እሁድ እስከ ሌላ እሁድ
ግብዣ ተያይዟል ፍቅር ካንቺ አፀድ
እስከ እሁድ ሰውን መውደድ
ከምን አርጎ ይሆን
ልብሽን ያነጸው
ለከበበሽ ሁሉ
ፍቅር የሚለግሰው
አንቺ ልጅ አቀልሽን ልብሽና ቤትሽን የማትደብቂው
ፍቅር ካንቺ አፀድ ዳሱን ጥሎ ይኖራል
ከእሁዱ እስከ እሁድ
አይነጥፍም አይጎድልም ማጀትሽ ቢጠጡ ቢበሉ
እስከ እሁድ ሰው እንዲ መውደድ
እንዴት ብሎ ያንን ሁሉ አባብሎ
ስስት አይነካካሽ እስከ እሁድ
ምን እንደሚተካሽ ... እስከ እሁድ
ዳር ይደርሳል እጇ . እስከ እሁድ
የሁሉም ነው ደጇ . እስከ እሁድ
ከእሁዱ እስከ እሁድ . እስከ እሁድ
እኔ እሷን መውደድ . እስከ እሁድ
ግብዣ ከሷ አፀድ . እስከ እሁድ
ለጉድ ነው ለጉድ . እስከ እሁድ
እስከ እሁድ. እስከ እሁድ . እስከ እሁድ
ሰው አይጠፋም ቤትሽ
ከእሁድ እስከ ከእሁድ
ዳስ ጥለሽበታል ላንድም ቀን ላይወርድ
ያላየሽ አይድንም ቀና አይሆንም ቀኑ
የሚል አዋጅ አለ እስኪመስል ሙሉ
አይነጥፍም አይጎድልም ማጀትሽ ቢጠጡ ቢበሉ
እስከ እሁድ ሰው እንዲ መውደድ
እንዴት ብሎ ያንን ሁሉ አባብሎ
ከአንድ እሁድ እስከ ሌላ እሁድ
ግብዣ ተያይዟል ፍቅር ካንቺ አፀድ
እስከ እሁድ ሰውን መውደድ
ታናሽ እና ታላቅ ባይሰፍርም እቤቷ
የሷን ትንሽነት ሰማው ካንደበቷ
ወትሮም ዝቅ ያለ ነው
ከአጀብ ተነጥሎ ከፍ የሚለው
እረ ያንቺስ ስራ ቀን ለሊሌ ይተጋል ፍቅርን ሲዘራ
ከአንድ እሁድ እስከ ሌላ እሁድ
ግብዣ ይዟል ፍቅር ካንቺ አፀድ
ስስት አይነካካሽ እስከ እሁድ
ምን እንደሚተካሽ . እስከ እሁድ
ዳር ይደርሳል እጇ . እስከ እሁድ
የሁሉም ነው ደጇ . እስከ እሁድ
ከእሁዱ እስከ እሁድ . እስከ እሁድ
እኔ እሷን መውደድ . እስከ እሁድ
ግብዣ ከሷ አጸድ . እስከ እሁድ
ለጉድ ነው ለጉድ . እስከ እሁድ
እስከ እሁድ. እስከ እሁድ . እስከ እሁድ



Авторы: Gossaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Single Collections
Альбом Single Collections
дата релиза
20-12-2018




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.