Gossaye Tesfaye - Yeged Sew текст песни

Текст песни Yeged Sew - Gossaye Tesfaye



ምነውውን
የግድ ሰው ካልተረዳኝ ካላወቀኝ ብዬ
ውስጤን ከፍቶ የሚያይልኝ ካልተገኘ ብዬ
አልደክምም ከንግዲህ ይብቃኝ የሰው ነገር
በል ልቤ ተመከር
አንቺም ደልቶሽ እንዳትኖሪ በፍቅር ከኔ ጋር
እኔም ደልቶኝ እንዳልልሽ አንቺ የህይወቴ አጋር
እንደቀልድ እንዳይሸሽ ፍቅራችን ከእውነቱ
አስቢበት እቱ
ስንጓዝ በፍቅር ተያይዘን ነበር እጅ ለእጅ
የጀመርነው መንገድ መጨረሻው ለየቅል ሆነ እንጂ
አንድ ነገር አለ የጋረደን ሃቁን ያሳተን
በመዋደድ ፋንታ ያራራቀን ልዩነት ፈጥረን
አልቻልንም መልመድ መተያየት
አንድ ቤት ሆነን
ወይ እዳዬ
ግድ የለም ያለ ነው
ወይ እዳዬ
ወትሮም ይታወቃል
ወይ እዳዬ
ሁለት ገዢ አንድ ቤት
ወይ እዳዬ
መቼስ ኖሮ ያውቃል
ወይ እዳዬ
ጊዜን አልሞግተው
ወይ እዳዬ
አልቀድመው ታግዬ
ወይ እዳዬ
ህልሜን ባንቺ
ወይ እዳዬ
አላየውም ብዬ
ምነውውን
የግድ ሰው ካልተረዳኝ ካላወቀኝ ብዬ
ውስጤን ከፍቶ የሚያይልኝ ካልተገኘ ብዬ
አልደክምም ከንግዲህ ይብቃኝ የሰው ነገር
በል ልቤ ተመከር
አንቺም ደልቶሽ እንዳትኖሪ በፍቅር ከኔ ጋር
እኔም ደልቶኝ እንዳልልሽ አንቺ የህይወቴ አጋር
እንደቀልድ እንዳይሸሽ ፍቅራችን ከእውነቱ
አስቢበት እቱ
ልሂድ በቃ እንግዲህ ለምናኔ ከምቀር ጓጉቼ
እርቅ እስክመሰርት ከውስጤ ጋር እራሴን አግኝቼ
አንቺም ሂጂ ይቅናሽ እወቂበት ካሆንኩሽ ወዳጅ
የግድ ይሁን ቢሉት መች ይሆናል ፍቅር በግዳጅ
አይታገሉትም መውደድን ይታደሉአል እንጅ
ወይ እዳዬ
የገመትነው ባይሆን
ወይ እዳዬ
ያለምነው ቢበተን
ወይ እዳዬ
የግዜ ጀግና እንጂ
ወይ እዳዬ
ወትሮም የሰው የለም
ወይ እዳዬ
ማንንም አልወቅስም
ወይ እዳዬ
የለም የምከሰው
ወይ እዳዬ
ያስጀመረን አምላክ
ወይ እዳዬ
ፈቅዶ ካልጨረስነው
ወይ እዳዬ
ግድ የለም ያለ ነው
ወይ እዳዬ
ሁለት ገዢ አንድ ቤት
ወይ እዳዬ
መቼስ ኖሮ ያውቃል
ወይ እዳዬ
ጊዜን አልሞግተው
ወይ እዳዬ
አልቀድመው ታግዬ
ወይ እዳዬ
ህልሜን ባንቺ
ወይ እዳዬ
አላየውም ብዬ
ወይ እዳዬ
ወይ እዳዬ
ወይ እዳዬ
ወይ እዳዬ



Авторы: Gossaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Single Collections
Альбом Single Collections
дата релиза
20-12-2018




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.