Текст песни




መፈለግ እኔን ያምረኛል
ከዳር ላልደርስ ሠምሮ ላይተዉ ያየኛል
መጨነቅ ልቤን ያፀናል
መደነቅ እጄን ያቀናል
ወይ ጎኔን ወጋሁት በቃል
እዉነቱ ከእርሱ ይልቃል
ጥርሴም ዳግም ይስቃል
መጨነቅ ልቤን ያፀናል
መደነቅ እጄን ያቀናል
ሃቅ ሆኖ እንደ ሠማይ ግልጽ የለዉ ጥበት
ደማቅ ሆኖ እንደ ፀሃይ ቢሸፍነዉ ዉበት
እርቃን ሆኖ ይቀራል ከእዉነቱ እስክንሄድ
ግብዝ ልብ ንቆ ይሆናል የእዉነትን ነገር
ህልመኛው እስኪነቃ ከእስሩ ሰንበር
ቅጣት ሆኖ ይቀራል ከእዉነቱ እስክንሄድ
እኔ እጠብቃለሁ
የቁና ዑደት ነዉ
ህልሙን የማረረዉ
ዘዉግ እና ዉበት ነዉ
ቀልቡን የጋረደዉ
ላይደርሰዉ ሰንቆ ነዶዉም አረረ
ነዶም አረረ
እኔ እጠብቃለሁ
የቁና ዑደት ነዉ
ህልሙን የማረረዉ
ዘዉግ እና ዉበት ነዉ
ቀልቡን የጋረደዉ
ላይደርሰዉ ሰንቆ ነዶዉም አረረ
ነዶም አረረ
እኔ እጠብቃለሁ
መፈለግ እኔን ያምረኛል
ከዳር ላልደርስ ሠምሮ ላይተዉ ያየኛል
መጨነቅ ልቤን ያፀናል
መደነቅ እጄን ያቀናል
ወይ ጎኔን ወጋሁት በቃል
እዉነቱ ከእርሱ ይልቃል
ጥርሴም ዳግም ይስቃል
መጨነቅ ልቤን ያፀናል
መደነቅ እጄን ያቀናል
እኔ እጠብቃለሁ
ጥርሴም ዳግም ይስቃል
እኔ እጠብቃለሁ
እዉነቱ ከእርሱ ይልቃል
እኔ እጠብቃለሁ
ከዳር ደርሶ ሠምሮ ያየኛል
እኔ ጠብቅያለሁ
ቀናዉ ለእኔ ሆኗል!!!



Авторы: Fikru Semma


Laeke - Bahire Tibeb
Альбом Bahire Tibeb
дата релиза
27-08-2024




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка