Meskerem Getu - Antema Geta Neh текст песни

Текст песни Antema Geta Neh - Meskerem Getu




አንተማ ጌታ ነህ እኔ ባገኝ ደግሞም ባጣም
አልጠረጥርህም ባጋጠመኝ እድል እጣ
አንተማ ጌታ ቢሆልኝ ባይሆንልኝ
አባ ወድሃለሁ ካንተ ፍቅር ማን ይለየኝ
አዝ፡-ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ለዘላለም ልገዛልህ
የትኛዉም ዉጣ ዉረድ በመንገዴ ገብቶ
አንተን እንዳልከተልህ አያደርገኝ ከቶ
ለክብርህ መገዛቴን ጠብቄ ቆማለሁ
ነገሮች ቢለዋወጡም አንተ ያዉ ነህ አዉቃለሁ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ለዘላለም ልገዛልህ
ለልጅ የሚያስፈልገኝን አባቴ ታዉቃለህ
ለዉሳኔህ የእኔን ምክር መች ትፈልጋለህ
በከፍታ ብታስኬደኝ በብዙ ብሳካ
ጌታዬ አንተ ብቻ ነህ በድል ያራመድከኝ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ለዘላለም ልገዛልህ
ተማምኜሀለሁ ጌታ እስከ ዘላለሜ
በጎ ነዉ ሐሳብህ ለኔባይሆን እንኳን ሕልሜ
መሻቴ ባይሞላልኝ ልቤ ባንተ ረካ
ሁሌም የህይወቴ ጌታ ነህ በማንም አትተካ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታዎች አይቀይሩክ
አንተማ ጌታ ነህ አንተማ ጌታ ነህ
አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታ ማይለዉጥህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ኸረ አንተማ ጌታ ነህ
ኧረ አንተማ ጌታ ነህ ሁኔታ ማይለዉጥህ





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.