Sami Dan - Yagere Lij текст песни

Текст песни Yagere Lij - Sami Dan



ሳሚ ዳን
ኤንዲ ቤተ ዜማ
ያገሬ ልጅ
የት ላግኝሽ ፈልጌ
ያገሬ ልጅ
አንቺ አብሮ አደጌ
ያገሬ ልጅ
ከሀሳቤ አልጠፋም እያልሽኝ
አስጨነቅሽኝ
ጉዦው ያኔ አስጨናቂ ነበር
ለኛ አይነቱ ባገር ለመኖር
ወጣት ነበርኩ እሳት የሞላኝ
ትትፈኛ ሰው ስወጣ ካገር
ስሰናበትሽ ትዝ ይለኛል
እንባ ካይኔ እየፈሰሰ
ያንቺማ ምኑ ይወራል
ልብሽ በሃዘን እየታመሰ
ሰው ሀገር ላይ የትዝታሽ ሞገድ
ይጠራኛል
ከሳሩ መስክ የዋሽንቱ ድምፅ
ይሰማኛል
የተነሳን ልብ ያላረፈ
ጭራሽ ብሎ ፍቅር የያዘው
እንቅልፍም የለው ጭንቀት ጧት ማታ
ክፉ ናፍቆት እየወዘወዘው
ያገሬ ልጅ
የት ላግኝሽ ፈልጌ
ያገሬ ልጅ
አንቺ አብሮ አደጌ
ያገሬ ልጅ
ከሀሳቤ አልጠፋም እያልሽኝ
አስጨነቅሽኝ
ጊዜው ሮጦ ሳናስበው
አመታት አለፉ ሳንተያይ
ዛሬም ድረስ ፍቅርሽ ሀያል ነው
እያባከነኝ ከታች ወደ ላይ
በጠፍ ጨረቃ ደጃፌ ላይ
በጠፍ ጨረቃ ደጃፌ ላይ
አንጋጥጬ አማትራለሁ
ወጋገኑ ላይ ምስልሽ ተስሏል
ባየው ባየው መች እጠግባለሁ
በሩ ሁሉ የተዘጋ ነው እንዳልመጣ
ለኔ ያለው አዲስ ብሩህ ቀን እስኪመጣ
ጠንከር በይ ውዴ አንቺዬ
ከፊታችን ተስፋ አለና
እሱ ከላይ የፈቀደ ቀን አይሻለሁ
እንደገና
ያገሬ ልጅ
የት ላግኝሽ ፈልጌ
ያገሬ ልጅ
አንቺ አብሮ አደጌ
ያገሬ ልጅ
ከሀሳቤ አልጠፋም እያልሽኝ
አስጨነቅሽኝ
ያገሬ ልጅ
ያገሬ ልጅ
እሱ ከላይ የፈቀደ ቀን አይሻለሁ
እንደገና
እሱ ከላይ የፈቀደ ቀን አይሻለሁ
እንደገና
እሱ ከላይ የፈቀደ ቀን
እሱ ከላይ የፈቀደ ቀን



Авторы: Sami Dan


Sami Dan - Keras Gar Negeger
Альбом Keras Gar Negeger
дата релиза
01-05-2016




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.