Mesfin Gutu - Alisham Lyrics

Lyrics Alisham - Mesfin Gutu




በረሃብ ቀጠና አይደለሁም እኔ
ልምላሜ ረግፎ አልገደለኝ ጠኔ
በአረንጓዴው ገነት ምንጭ በሚፈልቅበት
እንድኖር ተፈርዷል በኢየሱስ ዳኝነት
አዝ፦ አልሻም ከአንተ ውጭ ብልጭልጩን ዓለም
በቅቶታል ያልቤ አልፈልግም ዳግም(፪x)
አልፈልግም ዳግም
አልፈልግም ዳግም (እምቢ)
ለምንድን ነው አሉኝ ክርስትያን የሆንከው
ሁልጊዜ ኢየሱስ ኢየሱስ ምትለው
እስቲ ልንገራችሁ ይህንን ሚስጥር
. (2) .፡ አይሎ ነው የመስቀሉ ፍቅር
በቅቶታል ያልቤ አልፈልግም ዳግም(፪x)
አልፈልግም ዳግም
አልፈልግም ዳግም (እምቢ)
ነፍሴ አዋጅ ሰምታ የሞትን ቀጠሮ
ፍጥረት ሲያወራ የሽንፈት እሮሮ
ሕይወት ያበዛልኝ ማነው ከተባለ
አዳኙ ኢየሱስ ነው በዙፋኑ ያለ
አዝ፦ አልሻም ከእርሱ ውጭ ብልጭልጩን ዓለም
በቅቶታል ያልቤ አልፈልግም ዳግም(፪x)
አልፈልግም ዳግም
አልፈልግም ዳግም (እምቢ)
እስግዲህ በኢየሱስ ተደላድያለሁ
ዓለም የማይሰጠውን ሰላም አግኝቻለሁ
ታዲያ ለምን ልሩጥ ለምን ልቅበዝበዝ
እስቲ በኢየሱስ ላይ እርፍ ልበል
እርፍ እርፍ እርፍ እርፍ ድግፍ
ጥግት ጥግት



Writer(s): Mesfin Gutu



Attention! Feel free to leave feedback.
//}