Meskerem Getu - Lene Yaleh Tikuret paroles de chanson

paroles de chanson Lene Yaleh Tikuret - Meskerem Getu




ለኔ፡ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል
ለኔ ያለህ ምህረት ያስደንቀኛል
ለኔ ያለህ ትዕግሥት ያስገርመኛል
ለኔ ያለህ ትኩረት ያስደንቀኛል
መተላለፌን ደምስሰህ ተቀበልከኝ
በመንገዴ እንድጠፋ መቼ ተውከኝ
ከፊቴ ሆነህ እግሮቼን የምትመራ
ስጋቴን ሰብረህልኛል እንዳልፈራ
በጎ ስጦታ ፍፁም በረከት
ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል በምህረት
በነፍስህ የገዛሃት ይቺ ነፍሴ
ምሥጋናህን አትረሳም ሁልጊዜ
ለኔ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል
ለኔ ያለህ ምህረት ያስደንቀኛል
ለኔ ያለህ ትዕግሥት ያስገርመኛል
ለኔ ያለህ ትኩረት ያስደንቀኛል
የውስጤን ነገር ምነግርህ የማወጋህ
ልቤ በአንተ ተማምኖ ተረጋጋ
አሳረፍከኝ ወደ እኔ ተመልክተህ
ጩኸቴን የሚሰማ ማን እንዳንተ
በጎ ስጦታ ፍፁም በረከት
ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል በምህረት
በነፍስህ የገዛሃት ይቺ ነፍሴ
ምሥጋናህን አትረሳም ሁልጊዜ





Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.