Meskerem Getu - Tesemi Neh paroles de chanson

paroles de chanson Tesemi Neh - Meskerem Getu



ተሰሚ ነህ በሰማይ በምድር
ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክልህ
የፈጠርከን እንሰግድልሃለን
ሞገስህን ክብርህን እያየን
ይሹሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ
በደመናት ላይ እንደሚሄድ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ኧረ እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ኧረ እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም
ዘመንህ ዘላለም ከቶ አታረጅም
አምሳያ የለህም መቼም አትተካም
አዬዬ መቼም አትተካም
ፊትህ እንደ ፀሐይ በኃይል የሚያበራ
ክዋክብት ጨረቃን ደመናን የሰራህ
አዬዬ ፀሐይን የሰራህ
የአማልክቱ አምላካቸው ነህ
የፍጥረት ገዢ የዓለማት ንጉሥ ነህ
ወሰን የሌለህ ስራህ ረቂቅ
የማትታወቅ የሆንህ እጅግ ታላቅ
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም
ተሰሚ ነህ በሰማይ በምድር
ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክልህ
የፈጠርከን እንሰግድልሃለን
ሞገስህን ክብርህን እያየን
ይሹሩን ሆይ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ
በደመናት ላይ እንደሚሄድ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ኧረ እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
ኧረ እንደርሱ ያለ ቢፈለግም የለም
የዓለም ሁሉ መሪ ብርቱ ነህ ኃይለኛ
ከሁሉ ቀዳሚ የሌለህ ፊተኛ
አዬዬ የሌለህ ፊተኛ
ይሁን ባልከው ቃልህ ሁሉ ተፈጠረ
እቅድህ ግሩም ነው ስራህም ያማረ
አዬዬ ስራህም ያማረ
የአማልክቱ አምላካቸው ነህ
የፍጥረት ገዢ የዓለማት ንጉሥ ነህ
ወሰን የሌለህ ስራህ ረቂቅ
የማትታወቅ የሆንህ እጅግ ታላቅ
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም
እንዳንተ ያለ ቢፈለግም የለም
ኧረ እንዳንተ ያለ አይኖርም ዘላለም





Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.