Teddy Afro - Des Yemil Sikay paroles de chanson

paroles de chanson Des Yemil Sikay - Teddy Afro



ከሚገባሽ በታች ከምችለው በላይ
እስኪወድሽ ልቤ ደስ በሚል ስቃይ
ፍቅር ካንቺ ይዞ አየደጋገመኝ
ብወድሽ ብወድሽ አልሰለችህ አለኝ
ከሚገባሽ በታች ከምችለው በላይ
እስኪወድሽ ልቤ ደስ በሚል ስቃይ
ፍቅር ካንቺ ይዞ አየደጋገመኝ
ብወድሽ ብወድሽ አልሰለችህ አለኝ
ብናገር ማን ሰው ያምነኛል
ፍቅር አቅም ከልክሎኛል ግን እኔ አሄ
ደጋገመኝ ደጋገመኝ
ስንቴ ወግቶ ስንቴ አከመኝ አሄ
ልቤ ደጉ ልቤ ገሩ
የሰመጠው ከባህሩ አሄ
ምን ይዞ ነው ለመንገዱ
እንዲ ርቆ ሰው መውደዱ
አሀሀሀሀ
አዛኝ ሳይሆን ሰው ለራሱ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
አስበልጦ ከአንድ ነፈሱ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
እንደሚወድ ካቅሙ በላይ
አየሁ እኔስ ባንቺ ስቃይ
ልቤ ለኔ ማሰብ ትቶ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
ላንቺ ኖረ ባንቺ ሞቶ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
ይሄን ስቃይ በዚች አለም
የሚገልፀው ቃላት የለም
ቃል ከሌለው ቃላት መሳይ
ቃል ከሌለው ቃላት
አቃተኝ ብዬ ፍቅሬን እንዴት ላሳያት ጭንቄን
ቃል ከሌለው ቃላት መሳይ
ቃል ከሌለው ቃላት
አቃተኝ ብዬ ፍቅሬን አንዴት ላሳያት ጭንቄን
እንዴት ላሳያት ጭንቄን
እንዴት ላሳያት ጭንቄን
ኦሆሆሆ አይ አሀሀይ አሀሀይ አሄ
ከሚገባሽ በታች ከምችለው በላይ
እስኪወድሽ ልቤ ደስ በሚል ስቃይ
ፍቅር ካንቺ ይዞ አየደጋገመኝ
ብወድሽ ብወድሽ አልሰለችህ አለኝ
ብናገር ማን ሰው ያምነኛል
ፍቅር አቅም ከልክሎኛል ግን እኔ አሄ
ደጋገመኝ ደጋገመኝ
ስንቴ ወግቶ ስንቴ አከመኝ አሄ
ልቤ ደጉ ልቤ ገሩ
የሰመጠው ከባህሩ አሄ
ምን ይዞ ነው ለመንገዱ
እንዲ ርቆ ሰው መውደዱ አሄ
አሀሀሀሀሀሀ
ከፍ ካለው ሩቅ ሰማይ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
ዝቅ ካለው ጥልቅ ምድር
አዛኝ ሳይሆን ሰው
ከዚህ መሀል ወዶሽ ልቤ
ባንቺ ስቃይ መንገብገቤ
እስኪሰማኝ ነው ጉዳቱ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
ያንቺ ፍቅር ጤንነቱ
አዛኝ ሳይሆን ሰው
ይሄን መውደድ በዚች አለም
የሚገልፀው ቃላት የለም
ቃል ከሌለው ቃላት መሳይ
ቃል ከሌለው ቃላት
አቃተኝ ብዬ ፍቅሬን እንዴት ላሳያት ጭንቄን
ቃል ከሌለው ቃላት መሳይ
ቃል ከሌለው ቃላት
አቃተኝ ብዬ ፍቅሬን አንዴት ላሳያት ጭንቄን
እንዴት ላሳያት ጭንቄን (4)
አሀሀሀሀ አይ አሀሀይ አሄ
ቃል ከሌለው ቃላት መሳይ
ቃል ከሌለው ቃላት
አቃተኝ ብዬ ፍቅሬን እንዴት ላሳያት ጭንቄን
ቃል ከሌለው ቃላት መሳይ
ቃል ከሌለው ቃላት
አቃተኝ ብዬ ፍቅሬን አንዴት ላሳያት ጭንቄን
እንዴት ላሳያት ጭንቄን



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Tikur Sew
Album Tikur Sew
date de sortie
01-04-2012




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.