Teddy Afro - Hilm Aydegemem paroles de chanson

paroles de chanson Hilm Aydegemem - Teddy Afro



ህልም አይቼ ማታ ከማዶ መስኩ ላይ
ቁጭ ብለን ዋርካዉ ስር ፍቅርን ስንወያይ
የሚወድሽ ልቤ ገና አይቶሽ ሳይበቃዉ
በእጆችሽ ደባብሰሽ ልታቅፊኝ ስል ነቃው
ምናለ ባልነቃስ ከእንቅልፌ
እንዳድር በክንድሽ ታቅፌ
ብተኛ ተመልሼ እንዳልም
ለካ አንዴ ነዉ ህልም አይደገምም
የቤቴ ጓዳ አልጋ አንሶላዉ ትራሴ
አሳፍሮኝ ካንችዉ ዘንድ ደስ ሲላት ነፍሴ
ጎኔን ላመቻቸዉ ስገላበጥ ነቃው
የሚወድሽ ልቤ አልሞሽ ሳይበቃዉ
አዬ ድንገት ነቃሁ
የናፍቆቴን ረሃብ ካልጠገብኩሽ ስሜ
አይፈታም እና የሌሊቱ ህልሜ
ሳልም የእዉነቴን ነዉ እኔ አላዉቅም ዉሸት
ተይ መጥተሽ ደባብሽኝ ህልሜ እንዳይሆን ቅዠት
ኦሆይ
ኦሆሆኦሆይ
አሃ አሃሃሃአሃይ
አሃ አሃሃሃአሃይ
ህልም አይቼ ማታ ከማዶ መስኩ ላይ
ቁጭ ብለን ዋርካዉ ስር ፍቅርን ስንወያይ
የሚወድሽ ልቤ ገና አይቶሽ ሳይበቃዉ
በእጆችሽ ደባብሰሽ ልታቅፊኝ ስል ነቃው
ምናለ ባልነቃስ ከእንቅልፌ
እንዳድር በክንድሽ ታቅፌ
ብተኛ ተመልሼ እንዳልም
ለካ አንዴ ነዉ ህልም አይደገምም
ጭር ባለዉ ሌሊት ጨለማዉን ጥሶ
ይመለሳል ልቤ ካለሽበት ደርሶ
ቢርቅም ቅርብ ነዉ ያለሽበት ቦታ
ተኝቼ ሳልምሽ ምን ተሰማሽ ማታ
አዬ ባክሽ ማታ
ወፎች ሳይንጫጩ ሳሩ ሳይዝ ጤዛ
ተገኘሁ በህልሜ እዚህ ተኝቼ እዛ
ባሸለበዉ ሰማይ ስትናፍቂያት ነፍሴን
ወዳንቺ የሚያመጣኝ ህልም ነዉ ፈረሴ
ኦሆይ ኦሆሆኦሆይ አሃ አሃሃሃአሃይ
ኦሆይ ኦሆሆኦሆይ አሃ አሃሃሃአሃይ



Writer(s): Samuel Alemu, Theodros Kassahun


Teddy Afro - Tikur Sew
Album Tikur Sew
date de sortie
01-04-2012




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.