Gossaye Tesfaye - Akoyat текст песни

Текст песни Akoyat - Gossaye Tesfaye



እንደኔ እንደኖረች እንባ ሲፈሳት
ናፍቆት ሰው አገር እንዳስተከዛት
አይሳንህም ደግ ነህና
አይኗን አሳየኝ አቆያትና
አቆያት አቆያት አቆያት ልውደዳት
አቆያት ልውደዳት እሷንስ አቆያት
አቆያት አቆያት አቆያት ልውደዳት
አቆያት ልውደዳት እሷንስ አቆያት
ከዘመን ወለምታ ከማራያምደው
የሄዱትን አይተህ ያሉትን ኧረ ተው
አታምጣ ፈተና ባሳብ አትግደላት
ሰው ይዛለችና እሷንስ አቆያት
ከዛሬ ከነገ አካፍላ እየኖረች
አለች የልቤ ሰው እድሜ እየለመነች
ለኔ እሷን በጤና
ልያት አቆያትና
ለኔ እሷን በጤና
ልያት አቆያትና
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
እንደኔ እንደኖረች እንባ ሲፈሳት
ናፍቆት ሰው አገር እንዳስተከዛት
አይሳንህም ደግ ነህና
አይኗን አሳየኝ አቆያትና
አቆያት አቆያት አቆያት ልውደዳት
አቆያት ልውደዳት እሷንስ አቆያት
አቆያት አቆያት አቆያት ልውደዳት
አቆያት ልውደዳት እሷንስ አቆያት
ምንስ ሆድ ቢሞላ እህል ውሀ ተርፎ
ናፍቆት ያዘለ አንጀት መች ሊቀመጥ አርፎ
እያየሀት ግዜ አትለፋት እንደሰው
በል አሳያት አይኔን እንባዋን አብሰው
ለማሸነፍ ኑሮን ህይወት ግድ ሆነና
አራራቀን ከሰው ነጠለን ፈተና
ለኔ እሷን በጤና
ልያት አቆያትና
ለኔ እሷን በጤና
ልያት አቆያትና
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት
ለታመምኩላት ለተጎዳሁላት ለተወደስኩላት
ልክ እንዳምናው ዛሬም እኔው ልሙትላት



Авторы: Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Satamakhegn Bila
Альбом Satamakhegn Bila
дата релиза
04-02-2010




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.