Gossaye Tesfaye - Sew Telamdo текст песни

Текст песни Sew Telamdo - Gossaye Tesfaye



ከኔ ርቀሽ ለመሄድ ማሰብሽን
እንደ ሩቅ ሰው በድንገት ሰማሁና
እንዳልጠይቅሽ ደፍሬ አንቺን ደሞ
ምየልሻለው ወሬ እንደማልሰማ
ታድያ የቤቴን ገመና ማያቅ ሰው
ሲነግረኝ ሂድ ብዬ እንዴት ልመልሰው
ቀንቶ ነው አልል በቅርበት አያውቀኝም
ኧረ የሰማሁት ውሸት አይመስለኝም
እንድንነጋገር እስኪ አንዴ አረፍ በይ
ወደቤት ወደቤት የሚያስሮጠኝ ጉዳይ
ባንቺ አይደለም ወይ
እኔን ጥሎ መሄድ ታድያ አይከብድሽም ወይ
በፍቅር በመውደድ ያሳለፍነው ጊዜ እውነት አይደለም ወይ
(ልቤ ደሞ) ተሰቃይተህ በሷ (ልቤ ደሞ) ጭንቅ አትደርብብኝ
(ልቤ ደሞ) ቆይ ከሷ ይምጣ ልቤ ደሞ (ልቤ ደሞ) እስኪ አትቸኩልብኝ
ደርሶ አትዘንብኝ
(ልቤ ደሞ) የመንደሩን ወሬ (ልቤ ደሞ) አሳልፌ ለሷ
(ልቤ ደሞ) ብነግራት ታዝናለች ደሞ (ልቤ ደሞ) ሰው እንደማልሰማ
የማልኩላትን አስታውሳ
ከኔ ርቀሽ ለመሄድ ማሰብሽን
እንደ ሩቅ ሰው በድንገት ሰማሁና
እንዳልጠይቅሽ ደፍሬ አንቺን ደሞ
ምየልሻለው ወሬ እንደማልሰማ
ታድያ የቤቴን ገመና ማያቅ ሰው
ሲነግረኝ ሂድ ብየ እንዴት ልመልሰው
ቀንቶ ነው አልል በቅርበት አያውቀኝም
ኧረ የሰማሁት ውሸት አይመስለኝም
ልምዱ አለሽ አይደል ወይ ሲከፋሽ መናገር
እስኪ እንዴት በድንገት ማን አስተማረብኝ የሚያስደብቅ ነገር
ከኔ እንደምትርቂ ሲወራ ባገሩ
ኧረ እንዴት ኧረ እንዴት እሱ አልሰማም ብሎ ያማኛል መንደሩ
(ልቤ ደሞ) ተሰቃይተህ በሷ (ልቤ ደሞ) ጭንቅ አትደርብብኝ
(ልቤ ደሞ) ቆይ ከሷ ይምጣ ልቤ ደሞ (ልቤ ደሞ) እስኪ አትቸኩልብኝ
ደርሶ አትዘንብኝ
(ልቤ ደሞ) የመንደሩን ወሬ (ልቤ ደሞ) አሳልፌ ለሷ
(ልቤ ደሞ) ብነግራት ታዝናለች ደሞ (ልቤ ደሞ) ሰው እንደማልሰማ
የማልኩላትን አስታውሳ
ሰው ተላምዶ እንዴት ይጎዳል መሰለሽ መለየት ወዶ
ክፉ ቅጣት እንዴት ይጎዳል መሰለሽ አግኝቶ ማጣት
እያለው በቁሜ ከራቅሺኝማ
ምኑን ከምኔ ስትሄጅ ሊስማማ
ልትሄጅ ነው እንዴ ሰውነቴ አንቺን ለምዶ
ፍቅር አለሽ ከቤት ይቅር አትሂጂ ማዶ
እያለው በቁሜ ከራቅሺኝማ
ምኑን ከምኔ ስትሄጅ ሊስማማ
ልትሄጅ ነው እንዴ ጎኔ አንቺን ለምዶ
ፍቅር አለሽ ከቤት ይቅር አትሂጂ ማዶ



Авторы: Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Satamakhegn Bila
Альбом Satamakhegn Bila
дата релиза
04-02-2010




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.