Gossaye Tesfaye - Zim текст песни

Текст песни Zim - Gossaye Tesfaye



በቀረብኝ ምነው ባላነሳሁ እግሬስ ቢቀጣ ቀልቤ ቢሰበሰብ ቀድሞ
ለስሜቴ ከምሸነፍ ልቤ ረክቶ ላይረካ በእንባ ከሚታጠብ ታሞ
ለካ ለዚህ ነው የቀበጥኩት ለካ ለዚህ ነው
ለካ ለዚህ ነው የቀበጥኩት ለካ ለዚህ ነው
ባላወቅሁት ምነው ባላነሳሁ እግሬስ ቢቀጣ ቀልቤ ቢሰበሰብ ቀድሞ
ለስሜቴ ከምሸነፍ ልቤ ረክቶ ላይረካ በእንባ ከሚታጠብ ታሞ
ለካ ለዚህ ነው የቀበጥኩት ለካ ለዚህ ነው
ለካ ለዚህ ነው የቀበጥኩት ለካ ለዚህ ነው
በዲዮጋን ማሾ ያልተገኘች ወፍ
አትሁኚብኝ ባይሆን አብሬሽ ልክነፍ
አንቺ አልወጣሽ ካልጋ አላየሽ ሌላ ሰው
ይብላኝ ማለት እንጂ እንደኔ ላለ ሰው
እውነቱን ነግሬሽ (ወይኔ ወይኔ ወይኔ)
ሰምተሺው ከራሴ
አይልመድህ ብለሽ አዝነሽ ለመንፈሴ
ይቅር ስትይኝ ነው የምትረጋው ነብሴ
እንዲህ ከተባለ እናውጋ በምኩራብ
መቼም የዋህ ልብሽ መታገስ አያጣም
ተጎዳ አንድ በይው ልቤን በጣም በጣም
ዝም ዝም አለና ሊኖር
ዝም ዝም ክፉ እንዳልሰራ
ዝም ዝም መች ቻለ ልቤ
ዝም ዝም ዝምታን ፈራ
ዝም ዝም አለና ሊኖር
ዝም ዝም ክፉ እንዳልሰራ
ዝም ዝም አቃተው ልቤ
ዝም ዝም ዝምታን ፈራ
በቀረብኝ ምነው ባላነሳሁ እግሬስ ቢቀጣ ቀልቤ ቢሰበሰብ ቀድሞ
ለስሜቴ ከምሸነፍ ልቤ ረክቶ ላይረካ በእንባ ከሚታጠብ ታሞ
ለካ ለዚህ ነው የቀበጥኩት ለካ ለዚህ ነው
ለካ ለዚህ ነው የቀበጥኩት ለካ ለዚህ ነው
ቢያዳልጠኝ ስሜት እግሬን ለደቂቃ
ዛሬ አፍራለች ነብሴ ከፀፀት ማጥ ወድቃ
አንቺ አልወጣሽ ካልጋ አላየሽ ላለ ሰው
ይብላኝ ማለት እንጂ እንደኔ ላለ ሰው
እውነቱን ነግሬሽ (ወይኔ ወይኔ ወይኔ)
ሰምተሺው ከራሴ
አይልመድህ ብለሽ አዝነሽ ለመንፈሴ
ይቅር ስትይኝ ነው የምትረጋው ነብሴ
እንዲህ ከተባለ እናውጋ በምኩራብ
መቼም የዋህ ልብሽ መታገስ አያጣም
ተጎዳ አንድ በይው ልቤን በጣም በጣም
ዝም ዝም አለና ሊኖር
ዝም ዝም ክፉ እንዳልሰራ
ዝም ዝም መች ቻለ ልቤ
ዝም ዝም ዝምታን ፈራ
ዝም ዝም አለና ሊኖር
ዝም ዝም ክፉ እንዳልሰራ
ዝም ዝም አቃተው ልቤ
ዝም ዝም ዝምታን ፈራ
ዝም ዝም አልልም
ዝም ዝም አልልም
ዝም ዝም አልልም
ዝም ዝም አልልም እኔ
ዝም ዝም አልልም
ዝም ዝም አልልም እኔ
ዝም ዝም
ዝም ዝም
ዝም ዝም



Авторы: Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Satamakhegn Bila
Альбом Satamakhegn Bila
дата релиза
04-02-2010




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.