Gossaye Tesfaye - Chir Kalew Bota текст песни

Текст песни Chir Kalew Bota - Gossaye Tesfaye



ውስጤን ለማዳመጥ በዝምታ
እስኪ ልሂድ ደሞ ጭር ካለው ቦታ
ለልቤ ጓደኛ እራሴው ነኝ
ዛሬ ልስጠው ግዜ ላጫውተው ያጫውተኝ
ድንገት እንደነቃ እንደባነነ ግራ መጋባቴን የሚነግረኝ
አንዳንዴም ከራሴ ሳወራ ነው ከውስጤ ሰላም ጋር የሚያኖረኝ
ከሰው ጋር እየኖርኩ ሰው ከረሳኝ ውስጤ እንደ ዝምታ ሰሚ ካጣ
ታዲያ ለምን ብዬ አወራለው እራሴን በጩኸት እስክቀጣ
ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋኝ እንደሆን
(ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋው እንደሆን)
ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ
(ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ)
እንደ ቀላል እንጂ እንደ ብርቅ እንደ ብርቅ
አትቁጠረው ልቤ ተሰፍሮ ላያልቅ
ከዚህ አገር ጩኸት ከዚያ አገር ሁካታ
አረፍ እንበል ልቤ ጭር ካለው ቦታ
ልቤ እስኪ እረጋልቤ
አረፍ እንበል ልቤ
ውስጤን ለማዳመጥ በዝምታ
እስኪ ልሂድ ደሞ ጭር ካለው ቦታ
ለልቤ ጓደኛ እራሴው ነኝ
ዛሬ ልስጠው ግዜ ላጫውተው ያጫውተኝ
የዝምታን ቋንቋ ሰም ወርቁን የዝምታን ጥልቀት ሚስጥር ቃልን
ከራሱ የሚያወጋ ሰው ያውቀዋል ነፍሱን ያዳመጠ ልክ እንደ እኔ
ታዲያ እኔ መች ሆነ ሰው ጠልቼ ጭር ያለውን ስፍራ ያሶደደኝ
የመግባባት እርካብ ጥማት እንጂ የዝምታን መንገድ ያስመረጠኝ
ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋኝ እንደሆን
(ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋው እንደሆን)
ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ
(ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ)
እንደ ቀላል እንጂ እንደ ብርቅ እንደ ብርቅ
አትቁጠረው ልቤ ተሰፍሮ ላያልቅ
ከዚህ አገር ጩኸት ከዚያ አገር ሁካታ
አረፍ እንበል ልቤ ጭር ካለው ቦታ



Авторы: Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Альбом Siyamish Yamegnal
дата релиза
06-01-2019




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.