Meskerem Getu - Melesen Lyrics

Lyrics Melesen - Meskerem Getu



እንጀራ ልንበላ አልተከተልንህም
ሃብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም
ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋ
መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ
የዘላለም ሕይወት ማግኘታችን ጉዳይ
ሁሌም ብርቃችን ነው ከምን ጋር ሊተያይ
ሕይወት ያካፈልከን ኢየሱስ አንተ ነህ
ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ
ግን ዛሬ ሲመጣ በየአደባባዩ
ትኩረት የሚፈልግ የሚል እኔን እዩ
አንተን አደብዝዞ ራሱን የሚያጐላ
አባብሎ ወሰደን ሆነናል ተላላ
አቤቱ ሕዝብህን መልሰን
ሳንጠፋ ቀድመህ ድረስልን
አቤቱ ልጆችህን አስበን
ከድፍረት ከውድቀት ታደገን
በጐ በሚመስል ሃሳብ እየተሳበ
በመልካም ንግግር ሕዝብ ተሰበሰበ
ዓመጸ ማይከለክል የረሳ ፍርድህን
እራሳችንን እንዳናይ አደንዝዞ አሰረን
በዘመን ፍጻሜ ጫፍ ላይ ቆመን ሳለን
ልባችን እንዳያይ ምንው ተደለለ
ዘይታችንን እንሙላ ጊዜው ሳይገባደድ
ፈጥነን እንመለስ ከሄድንበት መንገድ
አቤቱ ሕዝብህን መልሰን
ሳንጠፋ ቀድመህ ድረስልን
አቤቱ ልጆችህን አስበን
ከድፍረት ከውድቀት ታደገን




Meskerem Getu - Mengistih Timta
Album Mengistih Timta
date of release
31-08-2016




Attention! Feel free to leave feedback.