Meskerem Getu - Semehn Ezemrewalehu Lyrics

Lyrics Semehn Ezemrewalehu - Meskerem Getu



ሥምህን እዘምረዋለው (፪x)
ዝናህን እዘምረዋለው
ሥምህን እዘምረዋለው
ኢየሱስ ኢየሱስ እላለሁ
ሥምህን እዘምረዋለው (፪x)
ኢየሱስ ኢየሱስ እላለሁ
አንተን እዘምርሃለው
ስላንተ መዝሙር እጽፋለው
ጌታ እዘምርሃለው
ሁልጊዜ ኢየሱስ እላለሁ
በጽድቅ መጠን እጅግ ከፍ ያልክ ነህ
ስምህ በምድር የተመሰገነ
ዝናህ ሁልጊዜ አስደናቂ ዜና
ወቅት የማይሽረው ዘላለም ገናና
ሥምህን እዘምረዋለው (፪x)
ኢየሱስ ኢየሱስ እላለሁ
ስላንተ ቆሜ አውጃለው
አንተን እዘምርሃለው
ስላንተ መዝሙር እጽፋለው
ጌታ እዘምርሃለው
በሥምህ ዜማ አወጣለው
ከቶ አይጨልምም በአንተ ፊት ጨለማ
ብርሃንነትህ ከጫፍ ጫፍ ይሰማ
ሞገስ ግርማህን ባውጅ ደጋግሜ
ቃሎች አነሱ የለህም ፍጻሜ
ሥምህን እዘምረዋለው (፪x)
ኢየሱስ ኢየሱስ እላለሁ
ስላንተ ቆሜ አውጃለው
አንተን እዘምርሃለው
ስላንተ መዝሙር እጽፋለው
ጌታ እዘምርሃለው
በሥምህ ዜማ አወጣለው
በሰማያት ያለኸው ልቀህ
በልቤ ላይ የተጻፍክ ደምቀህ
ጌታ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ
ለዓለም ሁሉ ስምህን ላውጅ
ሃሌሉያ (፮x)




Meskerem Getu - Mengistih Timta
Album Mengistih Timta
date of release
31-08-2016




Attention! Feel free to leave feedback.